የአየር በረራ አገልግሎቶችን በተመለከተ የተሰጡ ልዩ መመሪያዎች

የአየር በረራ አገልግሎቶችን በተመለከተ የተሰጡ ልዩ መመሪያዎች

አንድ የአየር በረራ አገልግሎት ተጠቃሚ ግለሰብ በረራው ከተሰረዘ ፤ ከዘገየ ፤ ከቀደመ ወይም ከበፊት የነበሩት ሁኔታዎች የተቀየሩ ከሆነ ፣ የተለያዩ ድጎማዎችንና ካሳዎችን እንዲቀበል ሕጉ ይፈቅድለታል በተጨማሪም ሕጉ ምን ዓይነት ካሳዎችንና ጥቅሞችን ግለሰቡ መቀበል እንደሚችል አስቀምጧል፣ ለምሳሌ የከፈለውን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ መመለስ ፤ የገንዘብ ድጎማ ፤ የዕርዳታም አገልግሎት ሊሰጥም ይችላል። በኮሮና ወረርሽኝ ጊዜ ልዩ ጊዜዊ ደንቦች ተዘጋጅተዋል ፤ ስለዚህ መብቶቹን በሙሉ እያንዳንዱን መመርመርና ድንጋጌውን ከጊዜው ጋር ማረጋገጥ ያስፈልጋል ።

ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መመሪያዎች ደግሞ ከእስራኤል ተነስተው ወደ ውጭ አገር ለሚደረጉ በረራዎች ፤ ወይም ወደ እስራኤል የሚደረጉ በረራዎች በትኬቱ ላይ እስካለው መድረሻ መውራጃ ቦታች ድረስ ፤ ከዚያ በመካከል አቁሞ እንደገና በረራ የሚደረግባችው በረራዎችን ("ግንኙነት") በዝርዝር ተቀምጠዋል ። ይህ መመሪያ በአገር ውስጥ በሚደረጉ በረራዎች ላይም ይሠራል

በዋናው ቲኬት ላይ ባልተካተቱ ሁኔታዎች በበራሪው ላይ ጉዳት ከደረሰ፣ ይህ ጉዳትም ተሳፋሪው ከሚከፈለው ገንዘብ ካሳ ዋጋ በበለጠ መጠን ጉዳት ከደረሰበት ፣ ተሳፋሪው በእያንዳንዱ ቡኔታ በተናጠል ይግባኝ ሊጠይቅ ይችላል ። ተሳፋሪው በሰዓቱ ለበረራ ሲደርስ ጥቅሞቹን የማግኘት ብቁነት ተጠበቀ ነው። "በጊዜ" ማለት በኩባንያው በተዘጋጀው ጊዜ፣ ነገር ግን ከበረራው ከሶስት ሰዓት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥና እንደዚህ ዓይነት ጊዜ ካልተያዘ፣ ቢያንስ አንድ ሰዓት ተኩል ከበረራ ጊዜ በፊት ማለት ነው። የተሰረዘ በረራ ከሆነ በሰዓቱ ለመድረስ ምንም ቅድመ ሁኔታ የለም።

የተለያዩ ካሳዎችን ወይም ድጎማዎችን ማግኘት ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ሁኒታዎችን ላይ ተግባራዊ አይሆንም

  1. በራሪው ወደ ሌላ በረራ አድራሻ የመዘዋወር ማስታወቂያ ከደረሰው ፤ በሌላኛው በረራ በመብረር በዋናው የበረራ ቲኬቱ ላይ በተገለጸው ቀን ካቀደው ቦታ ላይ ከደረሰ ፤
  2. ተሳፋሪው የበረራ ቲኬቱን በስጦታ ከተቀበለ ወይም ለሕዝብ ባልተሸጠው ልዩ ዋጋ፣ ነገር ግን ተሳፋሪው ቲኬቱን የወሰደው በአየር መንገዱ ወይም በበረራ አደራጅ ጥቅማ ጥቅሞች ፕሮግራም ("ነጥብ ፕሮግራም") አባልነት ምክንያት ከሆነ፣ ድንጋጌው ተግባራዊ አይሆንምና፣ ተሳፋሪው ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎች ሲሟሉ ጥቅማ ጥቅሞችን የማግኘት መብት ይኖረዋል።

የሚሰጡ ጥቅሞችና ማካካሻዎች

ከዚህ በታች ፤ ሕጉ መሰጠት አለባቸው ብሎ ያስቀመታቸውን ጥቅሞችና መካሻዎች በዝርዝር አስቀምጧቸዋል ።

የከፈሉትን ሙሉ በሙሉ መመለስ

የሚመለሰው የገንዘብ ብዛት ፤ ለበረራ የተከፈለውን ማንኛውም ክፍያ (የተከፈሉ ቀረጦችና በሕጉ መሰረት የተከፈሉ ሌላ ክፍያዎችን አጠቃልሎ) ፣ገንዘቡን በመመለሻው ቀን ፤ ገንዘቡ በተመልሽነት መቀበል አለብኝ ብሎ ካመለከተበት ቀን ጀምሮ በ 21 ቀናት ውስጥ ካሳው መከፈል አለበት ።

በረራ ወይም አገልግሎት በከፊል የተከናወነ ከሆነ ደግሞ ፤ የሚከተሉት መመሪያዎች ተፈጻሚ ይሆናሉ ።

  • በረራው ወደ መካከለኛ የበረራ ማቆሚያ ("ግንኙነት") ድረስ ከሆነ ፤ በራሪው ተመልሶ ወደ መጣበት የሚበርበትን ገንዘብ መቀበል አለበት ።
  • በረራው ሙሉ በሙሉ ወደሚበርበት ቦታ ከደረሰና የመመለሻው በረራ ካልተካሄደ ደግሞ ፤ ለበራሪው ግማሽ የሚሆን ማካካሻ ይገባዋል ።
  • ቲኬቱ የጉብኝትና የበረራው ዋጋ አብሮ የተካተተበት ከሆነና የቲኬቱን ዋጋ ለይቶ ለማወቅ ካልተቻለ ፤ መካካሻው የሚሰጠው የበረራውን እርቀት ፤ የበረራውን ዓይነት ፤ የተለያዩ አገልግሎቶችን ሒሳብ ውስጥ በማስገባት መከፈል አለበት፣ (ይህ መመሪያ ተግባራዊ የሚሆነውም ከወጣበት ቀን ጀምሮ ነው)፣

 

 

ዕርቀት   

የበረራ ዓይነትና ክፍሎች

እስከ 2,000 ሸቄል

እስከ 4,500 ኪሎ ሜትር

ከ 4,500 ኪሎ ሜትር የበለጠ

በትንንሽ የአየር አብራሪ ድርጅቶች የሚሰጡ በረራዎች / በቱሪስት ክፍል የሚደረጉ መደበኛ በረራዎች

830 ሸቄል

1,670 ሸቄል

2,780 ሸቄል

በቢዝነስ ክፍል ውስጥ የሚደረግ መደበኛ በረራ

2,220 ሸቄል

3,890 ሸቄል

6,950 ሸቄል

በመጀመሪያ ክፍል የሚደረግ መደበኛ በረራ

4,440 ሸቄል

7,790 ሸቄል

13,900 ሸቄል

የገንዘብ ማካካሻ

በራሪው የገንዘብ ማካካሻን የማግኘት መብት ካለው ፤ የሚደርሰው የማካካሻው ገንዘብ በታሰበው የበረራ ዕርቀት መሰረት እንደሚከተለው ይታሰባል ፤ (ይህ መመሪያ ከታተመበት ቀን ጀምሮ) ፤

 

የበረራው ዕርቀት

የማካካሻ ገንዘብ ብዛት

እስከ 2,000 ኪሎ ሜትር

1390 ሸቄል

እስከ 4500 ኪሎ ሚ/ር

2200 ሸቄል

ከ4500 ኪሎ ሜትር ከበለጠ

3340 ሸቄል

ካሳውን በረራው ከጀመረበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ቀናት ውስጥ በጥሬ ገንዘብ በባንክ ማስተላለፍ ፤ በቼክ ወይም ተሳፋሪው በጽሁፍ በተስማማበት በማንኛውም የመክፈያ መንገድ ይከፈላል ።

የዕርዳታ አገልግሎቶች

ተሳፋሪዎች ለእያገኙዋቸው የሚችሉትን የዕርዳታ አገልግሎቶችን በሚከተሉት ሁኔታዎች እንደሆኑ ሕጉ ይገልጻል

 

ምግብና መጠጦች

የመጠባበቂያ ጊዜን መሰረት በማድረግ

የመኝታ አገልግሎቶች

የአንድ ሌሊት ወይም ከዚያ በላይ ቆይታ የሚያስፈልግ ከሆነ ወይም ተጓዡ ካቀደው በላይ ረጅም ጊዜ አገልግሎትና መስተንግዶ የሚቀበል ከሆነ

የመጓጓዣ አገልግሎቶች

ከላይ ከተጠቀሰው ሆቴል ወይም ለተሳፋሪው እሩቅ ሳይሆን በተመጣጣኘ ዕርቀት ላይ ባለ ሌላ ሆቴል

የመገናኛ አውታር አገልግሎቶች

በተሳፋሪው ምርጫ መሰረት ፤ ሁለት የስልክ ጥሪዎችና የፋክስ መለዕክት ወይም ኢሜል መላክ የመረጠውን አገልግሎት መቀበል ይችላል

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ጥቅሞች ፤ የማካካሻ ሁኔታዎችንና ተሳፋሪው እንደ ሁኔታው ሊሰጠው የሚገባውን ጥቅሞችና የካሳ ዓይነቶች በዝርዝር ይቀርባሉ ፤

ይህን ካሳ ወይም ጥቅም ሊያስገኙ የሚችሉ ጉዳዮች

ከመጠን በላይ መመዝገብ ("ኦቨር ቡኪንግ")

በሕጉ መሰረት ፤ ከመጠን በላይ ምዝገባ ማለት ፤ ለበረራ ደህንነት፣ ለተሳፋሪው ጤንነት ወይም የቦታ እጥረት ወይም አስፈላጊ የሰነድ ደብዳቤ ዕጥረት ካለመኖሩ በስተቀር በትኬት ላይ የተጻፈውን የበረራ በራሪውን ለማሳፈር ፈቃደኛ አለመሆን ማለት ነው ። በዚህ ሁኔታ ፤ በራሪው የዕርዳታ አገልግሎቶችን የማግኘት መብት፤ ገንዘቡን ሙሉ በሙሉ መመለስ ወይም ሌላ አማራጭ የሆነ የበረራ ቲኬት (በተሳፋሪው ምርጫ) የማግኘት መብት አለው የገንዘብ መካካሻን ጨምሮ በራሪው ግለሰ በበረራ ሰዓቱ ከሶስት ሰዓት ቀደም ብሎ ከተገኘ

ሕጋዊ የጉዞ ሰነዶች ከያዘና የበረራ ፍቃድ ከደህንነት ምርመራው ጋር ማረጋገጫ ከያዘ፣ የደህንነት ምርመራውን አላልፍም ቢልም ቅሉ ከሚከፈለው የካሳ ገንዘብ ክፍያ መቀበል ግዳታ ነው ።

በራሪው ወደ ሌላ ተቀያሪ በረራ ላይ እጓዛለሁ ብሎ ከተስማማና የማረፊያ ሰዓቱ ከአራት ሰዓታት በላይ የማይዘገይ (እስከ 2,000 ኪሎ ሜትር የሚደርስ በረራ) ፤ አምስት ሰዓታት (እስከ 4,000 ኪሎ ሜት የሚደረጉ በረራዎች) ወይም ስድስት ሰዓት (ከ 4,500 ኪሎ ሜትር በላይ የሚደረጉ በረራዎች) የበራሪውን የመጨረሻ ማረፊያ ከመጀመሪያው የማረፊያ ቀን ጋር በማነጻጸር የሚቀበለው የካሳ ገንዘብ በግማሽ ይቀንሳል ።

የተሰረዘ በረራ

በረራው ከተሰረዘ ፤ አየር መንገዱ ድርጅት ወይም ለአጭር መንገድ የተከራየው የበረራ ኩባንያ በራሪው ወደ መጨረሻ ቦታው ላይ እንዲደርስ አማራጮችን መስጠት አለበት ። በረራው መሰረዙን የሚያረጋግጥ ማስታዎቂያ የማቅረብ ኃላፊነት ያለበት የበረራው ድርጅት ነው ።

የበረራ መቋረጥ በሚከሰትበት ጊዜ ተሳፋሪው ከአየር መንገዱ ኩባንያ የሚከተሉትን ጥቅሞች የማግኘት መብት አለው ፤ የዕርዳታ አገልግሎቶች ፤ የከፈለውን ገንዘብ መልሶ መቀበል ወይም ሌላ አማራጭ ቲኬት (በተሳፋሪው ምርጫ) በተጨማሪም የበረራውን ዕርቀት ግምት ውስጥ በማስገባት አስፈላጊውን የገንዘብ ማካካሻ በታቀደው መሰረት መቀበል አለበት ።

በራሪው ወደ ሌላ ተቀያሪ በረራ ላይ እጓዛለሁ ብሎ ከተስማማና የማረፊያ ሰዓቱ ከአራት ሰዓታት በላይ የማይዘገይ (እስከ 2,000 ኪሎ ሜትር የሚደርስ በረራ) ፤ አምስት ሰዓታት (እስከ 4,000 ኪሎ ሜት የሚደረጉ በረራዎች) ወይም ስድስት ሰዓት (ከ 4,500 ኪሎ ሜትር በላይ የሚደረጉ በረራዎች) የበራሪውን የመጨረሻ ማረፊያ ከመጀመሪያው የማረፊያ ቀን ጋር በማነጻጸር የሚቀበለው የካሳ ገንዘብ በግማሽ ይቀንሳል ።

 

በራሪው በሚከተሉት ሁኔታዎች ላይ የገንዘብ ካሳ የማግኘት መብት አይኖረውም

  1. ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ምክንያቶች በአንዱ ምክንያት በረራው ከተሰረዘ ፤

ሀ. ከአየር መንገዱም ድርጅት ቁጥጥር ውጪ የሆኑ ልዩ ሁኔታዎች ምክንያትና ድርጅቱ የተቻለውን ሁሉ ቢያደርግም በእነዚህ ልዩ ምክንያቶች በረራው እንዳይቋረጥ ማድረግ ካልቻሉ ።

ለ. የሥራ ማቆም ዓድማ

ሐ. የሰንበትን ወይም የበዓል ቀን መሻርን ለመከላከል

  1. ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መንገዶች በአንዱ መንገድ የበረራውን መሰረዣ ማስታወቂያ ለበራሪው የተሰጠ ከሆነ ፤

ሀ. ከታቀደው የበረራ ቀን ቢያንስ 14 ቀናት በፊት

ለ. ከታቀደው የበረራ ሰዓት ከ 7 እስከ 14 ቀናት ቀደም ብሎ ባለው ጊዜ ውስጥ ፤ የበረራው መድረሻ መለወጡን የሚያሳውቅ ማስታዎቂያ ለበራሪው ከደረሰና የበረራ ሰዓቶች ከአራት ሰዓት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ መሆን አለበት ።

ሐ. ከታቀደው የበረራ ሰዓት ከ 7 ቀናት ያነሰ ጊዜ ሲቀረው ሆኖም ግን ለበራሪው ተለዋጭ በረራ ተወስኖለት የበረራው ሰዓትም ከታቀደው የበረራ ሰዓት በአንድ ሰዓት የማይቀደም ከሆነ ። እንዲሁም፣ ከበራሪው  የመጨረሻ መድረሻ ቦታ ላይ አውሮፕላኑ የሚያርፍበት ጊዜ መጀመሪያ ከታቀደው የመድረሻ ጊዜ በኋላ ከሁለት ሰዓታት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ከሆነ

ሰ. የታቀደው ተለዋጭ በረራ ከበራሪው ጋር መጓዝ ለነበረባቸው በራሪዎች ሁሉ መቅረብ አለበት ። የቀረበው ተለዋጭ በረራ ተሳፋሪዎችን በሃይማኖት ፤ በጤንነትና በድሕንነት ፍተሻዎች መገደብ እንደሌለባቸው ማወቅ ያስፈልጋል ። 

የበረራ መዘግየት

  • በረራው ከሁለት ሰዓት በላይ የዘገየ ከሆነ ለበራሪው የምግብ ፤ የመጠጥና የመገናኛ አውታሮችን የማግኘት መብት አለው ።
  • በረራው ከአምስት ሰዓት በላይ ከስምንት ሰዓት በታች ባለው ጊዜ ውስጥ ከዘገየ ፤ በራሪው በመዘግየቱ ምክንያትና በራሪው ላለመብረር ከመረጠ ፣ ሙሉ የገንዘብ ተመላሽ ወይም ተለዋጭ ቲኬት የማግኘት መብት አለው ።
  • የበረራው ጊዜ ከዘገየና በረራው ለረጅም ጊዜ የሚካሄስ ስለሆነና በረራው በቀጣዩ ቀን የሚከናወን ከሆነ ለበራሪው መኝታንና የመጓጓዣ ትራንስፖርት አገልግሎት የመቀበል መብት አለው ።

ከላይ የተገለጸው እንዳለ ቢሆንም ፤ በሠራተኞች አድማ ወይ ሥራ ማቆም ምክንያት የበረራ መዘግየት ሲያጋጥም ለበራሪዎቹ የምግብ ፤ የመጠጥና የመገናኛ አውታሮችን ብቻ የመቀበል መብት አላቸው ።

በአገር ውስጥ የሚደረጉ በረራዎች

በአገር ውስጥ በረራ ከሦስት ሰዓት በላይ የተቋረጠ ወይም የዘገየ ከሆነ ፣ በራሪው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የካሳ መብቶች ማግኘት ይችላል ፤

 

ከቴል አቪቭ እስከ ቤን ጉሪዮን አየር ማረፊያ ወይም ከሀይፋ እስከ ኢላት ባለው የዕርቀት መስመሮች መካከል

270 ሸቄል

ከቴል አቪቭ እስከ ኤይን ያሃቭ ወይም እስከ ሮሽ ፒና (ማኻናይም) መካከል ባለው መስመር ላይ

160 ሸቄል

ሌላ ማንኛውም መስመር

220 ሸቄል

በረራውን ማስቀደም

በራሪው በረራው ስለቀደመበት በሚከተሉት ሁኔታዎች የተለያዩ ጥቅሞችንና ማካካሻዎች የማግኘት መብት ይኖረዋል ።

  • የበረራው ማስቀደሚያ ማስታወቂያ በቲኬቱ ላይ ከተገለጸው የበረራ ቀን ከ 14 ቀናት ባነሰ ጊዜ ውስጥ የተሰጠ ከሆነና፣ በረራው የቀደመው ከአምስት ሰዓት በላይ ወይም ከስምንት ሰዓት ያልበለጠ ከሆነ ፣ በራሪው ተመላሽ የገንዘብ ማካካሻ ወይም ሌላ የበረራ ቲኬት፣ የመረጠውን መቀበል ይችላል ።
  • ከስምንት ሰዓታት በላይ በቅድሚያ ከሆነ በራሪው ከሚከፈለው የገንዘብ ማካካሻ በተጨማሪ ተመላሽ ገንዘብ ወይም ሌላ አዲስ የበረራ ቲኬት የመቀበል መብት ይኖረዋል ።

የበረራ ቅድመ ሁኔታዎች ላይ ለውጥ ማድረግ

በራሪው የበረራ ሁኔታዎች ከተሻሻሉ (ወደ ከፍተኛ ክፍል ከተዘዋወረ) ተጨማሪ ክፍያ እንዲከፍል አይገደድም፤ ሆኖም ግን የበረራ ሁኔታዎችን ለበራሪው ወደ አልተመቹ ሁኔታዎች ከተቀየሩ (ወደ ዝቅተኛ የበረራ ክፍል ከተዘዋወረ) በራሪው ከ 60% - 100% የሚሆን የቲኬቱን ዋጋ ክፍያ እንደሚከተለው ያዝዛል ፤

 

የተቀየሩት ሁኔታዎች

የሚከፈለው የማካካሻ የገንዘብ መጠን

ከቢዝነስ የበረራ ክፍል ወደ ቱሪስት ክፍል መዘዋወር

በራሪው ከቲኬቱ ዋጋ 60% ይካሳል

ከቢዝነስ የበረራ ክፍል ወደ ቱሪስት ክፍል መዘዋወር

በራሪው ከትኬቱ ዋጋ 80% ይካሳል

ከመጀመሪያው የበረራ ክፍል ወደ ቱሪስት ክፍል መዘዋወር

በራሪው ከቲኬቱ ዋጋ 90% ይካሳል

ከ 4,500 ኪሎ ሜትር በላይ ከሆኑ በረራዎች ላይ፤ ከመጀመሪያው የበረራ ክፍል ወይም ከቢዝነስ የበረራ ክፍል ወደ ቱሪስት የበረራ ክፍል በረራ

 

በራሪው ከቲኬቱ ዋጋ 100% ይካሳል

በበረራው መካከል የሚደረጉ የዕረፍት ጊዜዎችን በተመለከተ የሚከፈለው የመካሻ ገንዘብ የበረሩትን የበረራ ዕርቀት ጋር በበማመጣጠን ይሆናል ። በረራው የጉዞ በረራ ከሆነ ደግሞ ፤ የመካካሻ ገንዘቡን ልክ በተመለከተ በገጽ 44 ላይ እንደተገለፀው ይሰላል

የማሳወቂያና የዕርዳታ ግዴታዎች

የበረራ ኃላፊ ድርጅቶችና አደራጆች በሕጉ በተደነገገው መሰረት የመንገደኞችን መብት የሚገልጹ ማስታወቂያዎችን በስፍራውና በድረ-ገጹ ላይ የማመላከት ግዴታ አለባቸው። በተጨማሪም በሕጉ መሰረት የጉዞ ኤጀንሲው እንደዚህ ዓይነት ማስታወቂያዎችን በድረ-ገጹ ላይ የማሳየት ግዴታም አለበት ። እንዲሁም በራሪው በሕጉ መሰረት መብቱን የሚገልጽ የተዘረዘረ የሰነድ ጽሁፍ ማግኘትና በአውሮፕላን ማረፊያው ውስጥ ለበራሪዎች መብታቸውን የሚያስከብርና ዝርዝር መረጃ የሚሰጥ ሠራተኛ መኖር አለበት ።

የሚከፈሉ የካሳ ዓይነቶች

አንድ በራሪ የሚያስፈልገውን የዕርዳታ አገልግሎት ካልተቀበለ ፤ የማካካሻ ገንዘቡ ካልተመለሰለት ፤ ፍርድ ቤት ቀርቦ እስከ 11,120 ሼቄል ድረስ የመካካሻ ክፍያ እንዲቀበል የመፍረድ ችሎታ ይኖረዋል ።

 

በዚህ የመምሪያ መጽሔት ውስጥ የቀረበው መረጃ አጠቃላይ መረጃ ብቻ ነው ፤ ግን ሕጋዊ ምክርን የሚተካ አይደለም እና ያለ ተገቢ ምክር ብቻዉን መታመን የለበትም.
ይህ መምሪያ ሰኔ ወር 2023 ዓ.ም. ያለውን መረጃ በሕጉ እና ደንቡ ላይ በመመርኮዝ ተሻሽሏል ።
አስገዳጅ የሚሆነው የሕጉ እና የደንቡ ጽሑፍ ነው።