ኃላፊነት
አከፋፋዩ ለተለያዩ ምርቶች የዋስትና ምስክር ወረቀት መስጠት አለበት ፤ ከእነዚህም ውስጥ አዲስ የኤሌክትሪክ፤ የኤሌክትሮኒክስ እና የጋዝ ምርቶች ለተጠቃሚው ዋጋቸው ከ 150 ብር በላይ ነው ። የወጡ ትዕዛዞች ፤ አከፋፋዩ የዋስትና አካል ሆኖ ሊያቀርበው የሚገባውን የአገልግሎት ዓይነት ፤ የዋስትና አቅራቢዎቹ ለተጠቃሚው ጥሪ ምላሽ መስጠት ያለባቸውን ቀናት ፤ ሸማቹ አገልግሎቱን ለማግኘት ቤት ውስጥ የሚቆይበትን ጊዜ የሚወስኑት ከሌሎች ነገሮች መካከል እነዚህ ናቸው። የሚመጡ ሠራተኞችና ሻጭ የመለዋወጫ ዕቃዎችን የመመለስ ግታዎች ናቸው ።
ምርቱን ለተጠቃሚው ከተረከበበት ጊዜ አንስቶ ወይም ምርቱ ከተጫነበት ቀን ጀምሮ ለአንድ ዓመት ዋስትና የመስጠት ግዴታ ያለባቸው ምርቶች አሉ ። እንዲሁም ደንቦቹ ከሽያጩ በኋላ ለሚደረገው አገልግሎት አዲስ የኤሌትሪክ ፤ የኤሌክትሮኒክስ እና የጋዝ ምርቶች ዋጋቸው ከ 150 ሼቄል በላይ የሆነ ደረጃን አስቀምጧል ። ቀደም ሲል በተጠቀሱት ደንቦች ውስጥ ፤ የአምራቹ ግዴታ ለሚመለከታቸው ምርቶች የመለዋወጫ ዕቃዎችን የማቅረብ ግዴታ ለተወሰነ ጊዜና በመተዳደሪያ ደንቡ ውስጥ በተቀመጡት ሁኔታዎች ውስጥ ተመስርቷል ። በእየሩሳሌም ፤ ቴል አቪቭ - ያፎ ፤ ሃይፋና ቤኤር ሼቫ ወይም በአቅራቢያቸው የሚገኙ የአገልግሎት ጣቢያዎችን የመንከባከብና በተወሰነ ጊዜ ውስጥ አስፈላጊውን የመጠገን ግዴታ አለበት ።
የዋስትና የምስክር ወረቀት ይዞ አንድን ምርት ለሸማች የሸጠ አከፋፋይ በምርቱ ላይ የሚለጠፍ ምልክት እንደሚለጠፍ ወይም ሸማቹ በምርቱ ላይ እንዲለጠፍ የሚለጠፍ ምልክት እንደሚሰጥ ተወስኗል። ይህም ቢያንስ ሙሉ የዋስትና ጊዜ የሚያበቃበትን ቀንና ሸማቹ ኃላፊነቱን ለመወጣት እንደ ቅድመ ሁኔታ የዋስትና የምስክር ወረቀት እንዲያቀርብ እንዳይገደድ መሆን አለበት ። ሸማቹ በመስመር ላይ እንዲያረጋግጥ እስከፈቀደ ድረስ አከፋፋዩ ከዋስትና ተለጣፊ ይልቅ ልዩ ተከታታይ መለያ ዘዴ ወይም መለያ ቁጥር ሊጠቀም ይችላል ። ክፍያን ወይም የጽሑፍ መልዕክትን ያላካተተ የስልክ ጥሪ ፤ በዋስትና ጊዜ ውስጥ ያለው ቀን እንደ መለያ ቁጥሩ ወይም ልዩ መለያ ቁጥሩና ተገልጋዩ እንደ ቅድመ ሁኔታና ዋስትናውን ለመጠቀም የዋስትና ሰር የምስክር ወረቀት እንዲያቀርብ አይገደድም ።
አንድ ሸማች ማንኛውንም ምርት ለመግዛት ሲያስብ ሻጩ ለምርት የሚሰጠውን የዋስትና የምስክር ወረቀት አስቀድሞ እንዲያይ ቢጠይቅ ጥሩ ነው ። በዚህ መንገድ በዋስትና ውስጥ ምን እንደሚካተቱና በውስጡ ያልተካተቱትን ማወቅ ይችላል ፤ ስለዚህ ምርቱን ለመግዛት ሲወስኑ ይህንን ከግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል ።
ከሽያጭ በኋላ ዋስትናን በተመለከተ እነዚህ መመሪያዎች አከፋፋይ በሕጉ መሰረት የመስጠት ግዴታ ካለበት ዋስትና ጋር እንደሚስማሙ መታወስ አለበት። ሻጩ በሕግ ከተደነገገው ጊዜ በላይ ለምርቱ የተራዘመ ዋስትና ከሰጠው በተራዘመ የዋስትና የምስክር ወረቀት ውስጥ የተቀመጡት ሁኔታዎች በተራዘመ የዋስትና ጊዜ ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ ። በአንፃራዊነት ረጅም የዋስትና ጊዜ ፤ ነጋዴዎች ሸማቾችን ከእነርሱ እንዲገዙ ለማሳመን እንደሚሰጡ ፣ እንዲሁም የፋይናንስ ትርጉም አለው ፤ ምክንያቱም ዋስትና በማይሰጥበት ለእያንዳንዱ ዓመት ሸማቹ ለብቻው መክፈል አለበት ። ስለዚያም ነው አገልግሎቱ ይህንን አኋዝ በምርቱ ዋጋ ግምት ውስጥ ማስገባት ተገቢ የሆነው፣ የመጨረሻውን ውሳኔ ሲያደርጉ ግምት ውስጥ ያስገቡ ። ይሁን እንጂ አንድ ሰው እንዲህ ዓይነቱ የተራዘመ ዋስትና በእርግጥ ጠቃሚ መሆኑን ወይም በተለያዩ ሁኔታዎች የተገደበ መሆኑን በጥንቃቄ ማረጋገጥ አለበት:: ኢኮኖሚያዊ የሚያደርገው (ዋስትናውን ለመከልከል ብቻ ፤ ለቴክኒሻኖች ጉብኝት ወይም ክፍሎች ክፍያ ማስከፈል ፣ ወ.ዘ.ተ.)።
አገልግሎትና ዋስትናን ተግባር ላይ ማዋል
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የቤት ውስጥ ምርቶችን በተመለከተ ጥገናቸው በሸማች ቤት ውስጥ እንደሚከናወን ይወሰናል። አገልግሎት ለመቀበል ጥሪው ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ ጥገናውን ለማጠናቀቅ የተወሰነ ጊዜ ይመደባል-:: መደበኛ ማቀዝቀዣዎችና በረዶ ሰሪ ማቀዝቀዣዎች (አንድ ቀን) ፤ የማብሰያ ምድጃዎች (ጋዝ) ፤_እና ኤሌክትሪክ ፤ ሁለት ቀናት) ፤ ዕቃ ማጠቢያና ማድረቂያ መሣሪያዎች ፤ የአየር ማቀዝቀዣዎች ፤ ማሞቂያ ምድጃዎች ፤ ማብሰያና መጋገሪያዎች ፤ መጠናቸው ከ 20 ኢንች በላይ የሆኑ ቴሌቪዥኖች ፤ የዕቃ ማጠቢያዎች ና የልብስ ማድረቂያዎች (ሶስት ቀናት) ።
የአገልግሎት መስጫው ቀን
ሕጉ እንዲህ ዓይነቱ ጉብኝት (ለመጓጓዣ ዓላማ ወይም ቀጣይነት ያለው አገልግሎት፣ ለክፍያ ምርቶች ጥገና ለማቅረብ ውል ካልሆነ በስተቀር) ከጠዋቱ 8:00 እስከ ምሽቱ 1:00 ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚሆን ይደነግጋል። በሳምንቱ ቀናት እስከ አርብ፣ በበዓል ዋዜማ እስከ ምሽቱ 1፡00 ሰዓት ድረስ በቅድሚያ ዝግጅት መሰረት። የጥበቃ ጊዜ ከተስማማበት ጊዜ ከሁለት ሰዓት በላይ መብለጥ የለበትም። በማስተባበር ቦታና በተጠቃሚው ፈቃድ አገልግሎት ሰጪው ለተጠቃሚው የስልክ ጥሪ እንዲጠብቅ ሊያቀርብ ይችላል። የጥበቃ ጊዜ ከሁለት ሰዓት በላይ ካልሆነ ፤ የአገልግሎት አቅራቢው የጉብኝቱን ቀን ከጠዋቱ 20፡00 ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ከስምምነት ጉብኝቱ ቀን ቀደም ብሎ ለሌላ ጊዜ ማስተላለፍና አዲስ ቀን ማስተባበር ይችላል። የአገልግሎት አቅርቦቱን ቀን ከተጠቀሰው ቀን በላይ ለሌላ ጊዜ ማስተላለፍ ይችላል ። በሕጉ መሠረት ያለው የአገልግሎቱ አቅርቦት፣
ለተጠቃሚው ማካካሻ
የሸማቾች ጥበቃ ሕግ እንደደነገገው ፣ ሸማቹ ከሁለት ሰዓታት ያለፈ ከተጠባበቀ የ 300 ሸቄል ካሳን ያገኛል ፤ ሆኖም ግን ከሶስት ሰዓትና ከዚያ በላይ ካለፉ የ 600 ሸቄል ካሳ የማግኘት መብት ይኖረዋል። ሻጩ ከስልክ ጥሪ ስምምነቱ በታቃራኒ ድርጊት ከፈጸመ፣ በ 300 ሸቄል ካሳ በሸማቹ ስምምነት ጋር ። ሻጩ ለተጠቃሚው በገንዘብ፤ በምርቶች ዓይነት ወይም በአገልግሎቶች ጋር ተመጣጣኝ የሆነ አማራጭ ማካካሻ ሊያቀርብ ይችላል። ሸማች መፍቀዱንና አለመፈቀዱን ማረጋገጫ ማስረጃ የማቅረብ ኃላፊነት ያለበት ሻጩ ብቻ ነው ።
የመዘግየቱ ሁኔታ የተፈጠረው በተለያዩ ምክንያቶች ከሆነ፣አገልግሎት ሰጪው የጉብኝቱን ቀንና ሰዓት ሲወስን ምክንያቶችን ያላወቀውና ስለእነርሱ ማወቅ ባልነበረበት ሁኔታ፣ ወይም አስቀድሞ ሳያይና ሊያያቸው ባልነበረበት ሁኔታ፣ ይህንም ሊግደው ስለማይችል፣ በዚህ ሁኔታ ሸማቹ ካሳ የመቀበል መብት የለውም። (ለምሳሌ፣ቴክኒሻኑ ሊመጣ ያልቻለበት ምክንያት) የመኪና አደጋ ከሆነ፣ሸማቹ የካሳ ክፍያ የማግኘት መብት አይኖረውም ።
በዚህ የመምሪያ መጽሔት ውስጥ የቀረበው መረጃ አጠቃላይ መረጃ ብቻ ነው ፤ ግን ሕጋዊ ምክርን የሚተካ አይደለም እና ያለ ተገቢ ምክር ብቻዉን መታመን የለበትም.
ይህ መምሪያ ሰኔ ወር 2023 ዓ.ም. ያለውን መረጃ በሕጉ እና ደንቡ ላይ በመመርኮዝ ተሻሽሏል ።
አስገዳጅ የሚሆነው የሕጉ እና የደንቡ ጽሑፍ ነው።