የተገዛው ቁሳቁስ ባለመግጠሙ ወይም ቁሳቁሱ ባለበት ጉድለት ምክንያት ግብይት መሰረዝ
ሸማቹ የገዛውን እያንዳንዱን ምርት ከተቀበለ በኋላ ወዲያውኑ የመመርመርና የማጣራት ግዴታ አለበት ። ሻጩም ለሸማቹ የገዛውን ምርት የመመርመር ዕድል የመስጠት ግዴታ አለበት ። ሸቀጡ የማይገጣጠም ወይም ጉድለት ካለው ወዲያውኑ ለድርጅቱ ማሳዎቅ ያስፈልጋል ። ለዓይን ጎልተው የሚታዩ ጉድለቶች ከሆነ ሸማቹ ጉድለቱን ለነጋዴው በወቅቱ ካላሳወቀ በነጋዴው ላይ መተማመን ብቻ አይችልም ። ከዓይን ድብቅ የሆኑ ጉድለት ከተከሰተ ደግሞ ፤ ገዢው ይህን ጉድለት እንዳወቀ ወዲያውኑ ለገዛበት ድርጅት ወዲያውኑ ማሳወቅ አለበት ። በሕጉ መሰረት አንድ ገዥ የተበላሸ ዕቃ ከገዛ ግብይቱን መሰረዝ ይቻላል ። ይህም የሚሆነው ማንኛውንም ግብይት እያንዳንዱን ሁኔታ በመመርመርና ሕጉን በመመርኮዝ ብቻ ይሆናል:: ስለዚህ በእንደዚህ ዓይነት ጉዳይ ከመድረሱ በፊት ማማከር ይመከራል ።
በስህተት ወይም ባለመግባባት ምክንያት ግብይትን የመሰረዝ መብት
ከዚህ በታች በሚዘረዘሩት አጋጣሚዎች ፤ በምርቱ ወይም በአገልግሎቱ ላይ ምንም ዓይነት ጉድለት ባይኖርም ሸማቹ በማንኛውም ምክንያት ግብይቱን የመሰረዝ መብት ይኖረዋል ።
የግብይት መሰረዣ ደንቦችን በመመርኮዝ ግብይቱን የመሰረዝ መብት
አንድ ሸማች ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ምክንያቶች የተለያዩ ምርቶችን ወይም አገልግሎቶች ከገዛ በኋላ ግብይቱን በመሰረዝ የከፈለውን ሙሉ ዋጋ እንዲመለስ በማድረግ መቀበል ይችላል ።
ከዚህ በታች ያለው ሠንጠረዥ ለተለያዩ አገልግሎቶች እና ምርቶችን የመሰረዣ ቀኖችን ይዘረዝራል ። ይህም በማስተዳደሪያ ደንቡ የተወሰነው ውሳኔ ተመርኩዞ ይሆናል ። ከዚህ በተጨማሪም የግብይይት ስረዛን ደንቦች በተመለከተ ይሆናል ።
የአገልግሎት / የምርት ዓይነት | የስረዛ ቀን እና ሌላም ገደቦች |
የቤት ዕቃዎች ፤ የቤትና የቤት ጓሮ ዕቃዎች የማይታሸጉ የምግብ ዕቃዎችን አያካትም ፤ ሰዓቶች ፤ በመብራት ኃይል የሚሠሩ መሳሪያዎች ፤ የኤክትሮኒክስ መሳሪያ፤ የውሃ ማጣሪያ እና የማዕድን ውሃን ማከፋፈያን ያካትታል ። | አንድ ሸማችምርትከገዛበ-14 ቀናትውስጥየታሸገበትን መክፈቱ እንደተጠቀመበት ወይም እንደተበላሸ አይቆጠርም፣ ሆኖም ግን ምርቱን ከመብራት ጋር ካያያዘውና በጋዝ ወይም በውኃ አማካኝነት አገልግሎት ላይ ካዋለው ልክ እንደተጠቀመበት ተደርጎ ይታያል ። |
ሸማቹ ዋና ማሸጊያቸውን ያልከፈታቸው የተለያዩ ምርቶች ፤ ምርቱ አልቆ ወይም እንደገና ድርጅቱ ማምረት ስላለበት ሸማቹ ምርቱ እንዲመጣለት አዝዞ ግን ምርቱን ለመቀበል በመጠባበቅ ላይ ካለ ፤ ይህ ግን ፤ የተገዙት ምርቶች በገዢም ጥያቄ መሰረት በትክክለኛ ዓይነታቸው የሚመረቱ ካልሆኑ ብቻ ይሆናል ። | ሸማቹ ዕቃውን ከተቀበለበት ቀን በ -14 ቀናት ውስጥ ። |
አልባሳት እና ጫማ ። | ከተገዛበት ቀን ጀምሮ እስከ 2 ቀናት ውስጥ ፤ ከዚያም በኋላ የዕረፍት ቀኖች ካልሆኑ በስተቀርና፣ በዕቃው ላይ ያለው የዋጋ መለያ እስከ አልወረደ ድረስ ። |
የእንግዳ ማስተናገጃ ፤ ሽርሽር ፤ የመዝናኛ እና የመደሰቻ አገልግሎቶች ፤ አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ ከእስራኤል ውጭ እንዲደረግ የታቀደ ካልሆነ በስተቀር (ከእስራኤል ከሚነሳ በረራ ወደ ውጭ አገር የሚደረገውን በረራ ጨምሮ ፣ ከእስራኤል ውጭ በሌላ አየር መንገድ የሚቀርብ አገልግሎቶች) ። ከእስራኤል ውጭ ሙሉ በሙሉ የሚሠራ አገልግሎትን በተመለከተ የመሰረዝ መብት አይኖርም:: አከፋፋዩ ከእስራኤል ውጭ ያለውን አገልግሎት የሚሰረዝበትን ስምምነት ከውል በፊት ለተጠቃሚው ካሳወቀ ብቻ ይሆናል ፤ ይህን ዕውነት ለማድረግ ማረጋገጫ ማቅረቡ በድርጅቱ ኃላፊነትላይ ይሆናል ። | ስምምነቱ ከተፈፀመበት ባሉት 14 ቀናት ውስጥ ሲሆን፣ ፣ስረዛው የሚፈቀደው ቢያንስ አገልግሎቱ ከተሰጠበት 14 ቀናት ውስጥ ከሆነ ነው ፤ እነዚህ ቀኖችም የዕርፈት ቀናትን አያካትቱም ። |
የተለያዩ ከሰዓት በኋላ የሚካሄዱ እንቅስቃሴዎች እና ሥልጠናዎች ፤ ይህም ሕጉ ያስቀመጠውን የፕሲኮሜትሪ ትምህርት ማስተማሪያ ቦታዎችን አያካትትም ። | ስምምነቱ ከተፈፀመበት ቀን ጀምሮ ባሉት 14 ቀናት ውስጥ ስምምነቱን መሰረዝ ይቻላል፣ ሆኖም ግን እነዚህ 14 ቀናቶች የእረፍት ቀናቶችን ማካተት የለባቸውም ። |
የውበት ሳሎኖችና የሰውነት ጥራት ጥበቃ እንክብካቤዎች ፤ የፀጉር ማስወገጃ ሕክምናን ጨምሮ፤ የረጅም ጊዜ የዕረፍት ጊዜ ስምምነት - ከአንድ ዓመት በላይ የሚቆይ ስምምነት ፤ ሸማቹ በዚህ ስምምነት ክፍያ አማካኝነት ከሚቀበላቸው አገልግሎቶች በተጨማሪ፣ ለሽርሽር የሚከፍፈሉ የዋጋ ቅናሾችን ወይም የተለያዩ ጥቅሞችን የመቀበል መብት ይኖረዋል: ወይም ደግሞ ፤ እነዚህን ጥቅሞች ሳያካትት የክለብ አባልነት ወይም ለክለብ ምዝገባ በሚከፈለው ክፍያ ቅናሽ ይኖረዋል ። በሕጉ መሰረት እነዚህ አገልግሎቶች የሚሰጡት በአገር ውስጥ ወይም ከአገር ውጭ የሥራ ሙያ ፈቃድ ባላቸው ባለሙያዎች ፤ የስልክ አገልግሎት ለመስጠት በአጠቃላይ ፈቃድ ወይም ልዩ የሆነ አጠቃላይ ፈቃድ ባለው ባለሙያ የሚሰጥ አገልግሎት ፤ የሬዲዮ አገልግሎቶችን ፤ የተንቀሳቃሽ ስልክን ለማቅረብ አጠቃላይ ፈቃድ ባለው ሰው የሚሰጡ አገልግሎቶች ፤ ይህም የሚመረኮዘው ሕግ ቁጥር 4ሀ ክፍል 2 ነው ። በአንቀጽ 414 - የመገናኛ አውታሮች ሕግ ሀ1 መሠረት የተሰጡ ልዩ ፈቃድ መሰረት የአንድ ድርጅት አባል ለመሆን ወይም ለመመዝገብ ፤ የጤና ነክ ክለቦችን፤ ጓደኛ ለመተዋወቅ ወይም ደግሞ የሎተሪ ደንበኛ የመሆንን ይመለከታል ። | ስምምነቱ ከተፈፀመበት ቀን ጀምሮ ባሉት 14 ቀናት ውስጥ ወይም በሸማቾች ጥበቃ ሕግ ቁጥር 13ሐ (ሐ) ላይ እንደተገለጸው የጽሁፍ ውል ወይም ሰነድ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ፤ የአገልግሎት አቅራቦቱ የቀን ገደብ ቢኖሩትም ቅሉ፣ የአገልግሎቱ አቅርቦት ለጥቂት ጊዜ ነው። |
በሻጩ አማካኝነት የሚደረጉ የአገልግሎትና የቁሳቁሶች ሽያጭ ፤ ይህም ዕጣ እንዲደርሰን የሚያጓጉ ሁኔታዎችን በመፍጠር ሻጩ ለመሸጥ የሚፈልጋቸውን ቁሳቁሶች ለመሸጥ መሞከር ። | ዕቃዎችን በሚገዙበት ጊዜ - ሸማቹ ዕቃውን ከተቀበለበት ቀን ጀምሮ በ -14 ቀናት ውስጥ ፤ የአገልግሎት ግዥን በተመለከተ - ግብይቱ ከተፈጸመበት ቀን ጀምሮ በ -14 ቀናት ውስጥ ወይም የጽሑፍ ውል ወይም ሰነድ የሸማቾች ጠበቂ ሕግ ክፍል 13ሐ (ሐ) ላይ እንደተገለጸው ይሆናል ። ከሁለቱም ዘግየት ያለው ይመረጣል ። ምንም እንኳን ግብይቱ የዕቃዎች ወይም የዕቃዎች ግብይት ባይሆንም፣ በተጨማሪም የተደረገው ግብይት ለተወሰኑ ጊዜያቶች ቢሆንም ፤ በሂደት የሚካሄዱ ግብይቶች - ግብይቱ ከተፈጸመበት ቀን ጀምሮ ባሉት 14 ቀናት ውስጥ እና አገልግሎቱ ከመጀመሩ በፊት ዕረፍት ያልሆኑ እስከ ሁለት ቀናት ድረስ ። |
በመጓጓዣ መ/ቤት ሕግ መሰረት ከመኪና አስመጪ የተገዛ አዲስ ተሽከርካሪ መክና ። | ግብይቱ ከተፈፀመበት ቀን ጀምሮ ባሉት 14 ቀናት ውስጥ በትራፊክ ደንቡ መሰረት በተጠቃሚው ስም እስካልተመዘገበ ድረስ። |
አንድ ጌጣጌጥ የተመደበለበት ዋጋ ከ 3000 አዲስ ሸቄል ያልበለጠ ። | ከግዢው ቀን ጀምሮ እስከ 2 ቀናት ውስጥ የዕረፍት ቀናት ካልሆኑ:: |
የመሰረዝ መብቱ የማይመለከታቸው ልዩ ሁኔታዎች
ይህ የመሰረዝ ሕግ ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት ዉሎች ላይ ተግባራዊ አይሆንም ፤ ከገዥው ቤት የተገጣጠሙ ዕቃዎች፤ ለገዢው ተብሎ በልዩ ሁኔታና እርሱ በልዩ ትዛዝ በፈለጋቸው መለኪያዎች የተሰሩ ዕቃዎች ፤ በተጨማሪም በሕጉ መሰረት መመለስ የማይቻሉ። ዕቃዎች ፤ የምግብ ምርቶች ፤ መድሃኒቶችና ለምግብ ተጨማሪ የሆኑ ክኒኖች ፤ ወደ ሻጩ ከመድረሳችን በፊት የመጠቀሚያ ጊዜያቸው የሚያልፍባቸው ፤ የተሰጠውን የሕግ መረጃ በመመርኮዝ ፤ ጋዝ መቅዳት ወይም ማባዛት የሚቻሉ ነገሮች ፤ በግልባጭ ሕግ መስራት የሚቻሉ ነገሮች ፤ ሸማቹ የመጀመሪያ ማሸጊያቸውን ከተከፈተ ፤ የውስጥ ልብስ ፤ ይህም የመዋኛ ልብሶችን በመጨመር ፤ ከ 3000 ሽህ አዲስ ሸቄል በላይ የተከፈለባቸው ጌጣጌጦች ፤ ይህ ግን የእጅ ሰዓትን አያጠቃልልም ፤ ገዢም የገዛቸውን ቁሳቁሶች ከስድስት ወር በኋላ እንዲያመጡለት ያመለከተ ከሆነ ፤ በስጦታ የሚሰጡ የመግዣ ካርዶች የተገዙ ቁሳቁሶች ።
የመስተንግዶ፣ የጉዞ፣ የመዝናኛ ወይም የመዝናኛ አገልግሎቶችን በተመለከተ ሙሉ በሙሉ ከእስራኤል ውጭ እንዲደረግ ነጋዴው ከኮንትራቱ በፊት ለተጠቃሚው ከገለጸ፣ከዚህ ጋር በተያያዘ፣ ከእስራኤል ውጭ ያለውን አገልግሎት አቅራቢውን ግብይት የሚሰረዝበትን ውል፣ የመሰረዝ መብት እንደ የግብይት ደንቦቹ መሰረዝ አይተገበርም፣ ነገር ግን ከእስራኤል ውጭ ያለው አገልግሎት አቅራቢው ግብይቱን የመሰረዝ ውል በእስራኤል ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፣ ሙሉ በሙሉ ከእስራኤል ውጭ እንዲደረጉ የታቀዱ የእንግዳ መስተንግዶ፣ የጉዞ፣ የመዝናኛ ወይም የመዝናኛ አገልግሎቶች ለምሳሌ ከእስራኤል ተነስቶ በሌላ አየር መንገድ ከሚሰጠው በረራ ጋር የሚያገናኝ በረራ፣ ወይም ከእስራኤል ውጭ ከበረራ በስተቀር የዕረፍት ጊዜ ፓኬጅ ናቸው። ከእስራኤል ውጭ ምንም የሚያገናኝ በረራ የለም።
ለተሰረዘ ግብይት የሚሰጥ ተመላሽ ገንዘብ
ግብይቱ በሕጋዊ መንገድ የተሰረዘ ከሆነ ፤ ሻጩ ሸማቹ የከፈለውን ገንዘብ ለተጠቃሚው መመለስ አለበት ። ሸማቹ ግዢውን የፈጸመው በሻጩ ሱቅ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት ፤ ይህንም ለማረጋገጥ የገዛበትን ደረሰኝ ፤ ከገንዘብ መክፈያ ማሽኑ የሚወጣና የከፈለውን ገንዘብ የሚያሳይ ጽሁፍ ያለበት ወረቀት ፤ የመቀየሪያ ወረቀት ማቅረብ አለበት። ሌላው የማረጋገጫ መንገድ ደግሞ ፤ ዕቃው የተገዛበትን ቀን ፤ ዋጋውንና የመክፍያ ዘዴውን የሚያሳይ ማረጋገጫ ወረቀት ማቅረብ አለበት ።
ሻጩ በተቻለው መጠን የግብይቱን በመሰረዝ ለገዥው የገዛበትን ገንዘብ መመለስ አለበት ። ለማንኛውም ግን ፤ ክፍያው ስምምነቱ ከፈረሰበት እስከ 7 የሥራ ቀናት የዘለለ መሆን የለበትም ፤ የሚመለሰው ክፍያም ገዢው በከፈለበት መንገድ ይሆናል ።
የስረዛ ክፍያዎች እና ተጨማሪ ጉዳዮች ፤ አከፋፋዩ ከተመላሽ ገንዘብ ለተጠቃሚው እንዲቀንስ የተፈቀደለት ምንድን ነው?
ሻጩ ገዢው ከገዛበት ዋጋ ምንም ማጉደል የለበትም ፤ ከሚከተሉት ልዩ ሁኔታዎች በስተቀር።
ስጦታ ሲቀበሉ የመሰረዝ መብት
በሕጉ መሠረት ፣ሸማቹ ምርቱን ካልገዛው ወይም አገልግሎቱን በቀጥታ ከነጋዴው ባይገዛም፣ ነገር ግን በስጦታ የተቀበለ ቢሆንም ፣የመሰረዝ መብቱ ሥራ ላይ እንዲውል ስጦታው (የመግዣ ካርድ ከሆነ ነው) የተቀበለበት የመቀየሪያ ወረቀት ፤ ውሉ እንደተከናወነ የሚያሳይ ሌላ የማረጋገጫ ፤ ዉሉ የተፈጸመበት ቀን የተከፈለው የገንዘብ ብዛት እና የክፍያው መንገድ ማሳየት አለበት ። ስጦታው የተገዛው በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በ - 5 የሥራ ቀናት ውስጥ በጥሬ ገንዘብ ወይም ካሽ በሆነ ቸክ ይመለሳል ፤ ስጦታው የተገዛው ገና ባልተከፈለ ቼክ ከሆነ ደግሞ ፤ ቸኩ ክፍያ ላይ ከሚውልበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ቀናት ውስጥ ይመለሳል ። ስጦታው የተገዛው በክሬዲት ካርድ ከሆነ ገቢው በጥሬ ገንዘብ ይመለሳል ፤ ይህም ስጦታውን የሚገዛው ሸማች ሒሳቡን እንዲከፍል ተወስኗል ።
የእርቀት ሽያጭ ግብይትን ስለመሰረዝ
የእርቀት ሽያጭ ግብይት ማለት ሻጩ እና ገዥው ፊት ለፊት የማይገናኙበት ማንኛውም ግብይት ሲሆን ፣ይህም በሩቅ የማስታዎቂያ ግብይት ሥራ ምክንያት የተደረገ ነው ። የእርቀት ግብይት ሂደት በፖስታ ፤ በስልክ ፤ በራዲዮ ፤ በቴሌቭዥን፤ የመገናኛ አውታሮች ፤ በፋክስ ፤ በትንንሽ መጽሔቶች፤ ማስታዎቂያዎች ወ.ዘ.ተ. ይህ ዓይነት ግብይት ገዥውና ሻጩ ፊት ለፊት ተገናኝተው ግብይቱን አለማድረግን ዓላማ በማድረግ ነው።
የእርቀት ሽያጭ ግብይትን በተመለከተ ሕጉ በነጋዴው ላይ የተለያዩ የግብይቶችን ዝርዝሮች በተመለከተ ሻጩ ማሳዎቅ አለበት። የሻጩ ዝርዝር ፤ የምርቱ ዓይነት ፤ ዋጋውንና የክፍያ ውሎችን ፤ ምርቱን የሚያስረክብበት ቀንና ዘዴ ፤ ሻጩ ስለሚያቀርበው ምርት አስፈላጊውን ዋስትና ማቅረብ ግዴታው ነው ። ይህ ዝርዝር የሕጉን ዝርዝር ሰነድ ማሳየትና አንድ ሸማች የገዛውን ዕቃ ለመመለስ ያሉትን መብቶች ማጠቃለልን ያስፈልጋል ።
የእርቀት የሽያጭ ግብይት ሲፈፀም ሸማቹ በማንኛውም ምክንያት በሚከተሉት ሁኔታዎች የመሰረዝ መብት ይኖረዋል ።
በእርቀት የሽያጭ ግብይት ውስጥ የስረዛ ክፍያዎች
ሸማቹ ያካሄደውን የእሩቅ የሽያጭ ግብይትን የሰረዘው በገዛው ዕቃ ላይ ባለበት ጉድለት ወይም የአለመመጣጠን ምክንያት ሳይሆን በገዥው ጸጸት ከሆነ፣ አከፋፋዩ ከሻጩ የ 100 ሸቄል ወይም ከገዛበት ዋጋ ላይ 5% ከሁለቱ ያነሰውን አንዱን በመምረጥ የስረዛ ቅጣት መቀበል ይችላል ።
የግብይት ውል የተሰረዘበት ምክንያት ምርቱን ወይም አገልግሎቱን በጊዜው ባለማቅረብ ፤ ስለ ምርቱ ወይም ስለ አገልግሎቱ የተሰጠው መግለጫና ለተጠቃሚው በተሰጠዉ መካከል ልዩነት ካለና በእነዚህ ምክንያቶች ውሉን ከተሰረዘ ፤ ገዥው የውል መሰረዣ ክፍያ እንዲከፍል አይጠየቅም ።
የእርቀት የሽያጭ ግብይት ከተሰረዘ፣ ሻጩ ለገንዘብ መክፈያው የባንክ ካርድ ድርጅት - ክሬዲት ካርድ ኩባንያው የተላከውን የክፍያ መሰረዣ ማስታወቂያ ደብዳቤ ቅጂ ለተጠቃሚው መስጠት አለበት ።
አንድ ሸማች ግብይቱን ሲሰርዝ የተቀበለውን ምርት ያለምንም ጉዳት መመለስ እንዳለበት ማስታወስ አስፈላጊ ነው ። በተሸመተው ምርት ላይ ከፍተኛ መበላሸት ምክንያት የምርቱ ዋጋ ከቀነሰ፣ ሻጩ ለደረሰበት ጉዳት ሸማቹን ሊከስ ይችላል ። ስለዚህ ምንም እንኳን ግብይትን ለመሰረዝ ከመወሰናችሁና ይህን ለማድረግም ሕጉ የሚፈቅድላችሁ ከሆነ፣ ምርቱን ወደገዛችሁበት ድርጅት እስክትመልሱ ድረስ አለመጠቀማችሁን አረጋግጡ ። ነገር ግን የምርት ማሸጊያውን መክፈት ብቻውን ግብይቱን የመሰረዝ መብትን አይጎዳውም። በሕግ ከተገለጹት ጉዳዮች በስተቀር ፤ ለምሳሌ ሊባዙና ቅጅ ሊሆኑ የሚችሉ ምርቶች ።
አገልግሎቱን መስጠት ከጀመረ በኋላ አገልግሎቱ ከተቋረጠ ሸማቹ ለአገልግሎት ላደረገው አንጻራዊ ጥቅም ለነጋዴው መክፈል አለበት ። ሻጩ በሸማቹ ቤት ውስጥ ልዩ ተከላ ከጫነ (ለምሳሌ በኬብሎች ወይም በሳተላይት የሚመለከቱ መሳሪያዎች) ከግብይቱ መሰረዣ ክፍያ በተጨማሪ ሻጩ የመጫኛ ወጪዎችን እስከ 100 ብር የመክፈል መብት ይኖረዋል።
ከእስራኤል ውጭ ለቱሪዝም አገልግሎቶች አቅርቦት የእርቀት የሽያጭ ግብይት መሰረዝን በተመለከተ የተሰጡ ልዩ መመሪያዎች
ከእስራኤል አገር ውጭ ሙሉ ለሙሉ የሚሰጠውን የቱሪዝም አገልግሎት የእርቀት ሽያጭ ግብይትን በተመለከተ ነጋዴው ለሸማቹ ከሁለት አማራጮች መካከል እንዲመርጥ ሊያቀርብ ይችላል ። በሸማቾች ጥበቃ ሕግ በተደነገገው መሰረት ለግብይቱ የመሰረዝ መብትን ወይም ከእስራኤል ውጭ ያለው የአገልግሎት አቅራቢው ድርጅቶች የስረዛ ፖሊሲን ።
ይህን አማራጭ ሽጩ ድርጅት በእርቀት ግብይት ወቅት ለሸማቹ ማሳዎቅ አለበት ፤ ዉሉን ከመፈረማቸው በፊት የስረዛ ፖሊሲን በተመለከተ ያለውን መረጃ ፤ ግብይቱን የመሰረዝ መብትን የሚያካትት መሆኑን በዝርዝር መግለፅ ፤ ከዚያም በተጨማሪ መሰረዝ የሚችልባቸው ቀኖችን ፤ ለመሰረዝ የሚከፈሉ ክፍያዎችንና ተመላሽ ገንዘብ የማግኘት ዕድል ያካተቱ መግለጫዎች መሆን አለባቸው ። እነዚህ ዝርዝሮች ሻጩ ለገዥው ከሚሰጠው ሰነድ ጋር መያያዝ አለባቸው ። እንዲሁም ፤ ሻጩ እነዚህን ዝርዝሮች በኢንተርኔት ድረ-ገጽ ጣቢያው ላይ ማሳዎቅ አለበት ። የስረዛ ፖሊሲን በተመለከተ ፤ ፖሊሲውን ለተጠቃሚው ይፋ ማድረግን ጨምሮ ፤ የማረጋገጥ ኃላፊነት የተጣለው በሻጩ ላይ ነው ።
ጥቂት ነጥቦችን ልብ ሊባል ይገባል
የሽያጭ ግብይት መሰረዝ፣
ይህ የሽያጭ ግብይት ፤ ሻጩ የመሸጭ አገልግሎቱን ያካሄደው በመደበኛ የመሸጫ ቦታው ሳይሆን በየቦታው እየተዘዋወረ ግብይት ሲያደርግ ማለት ነው ፤ ለምሳሌ ፤ በሸማቹ መኖሪያ ቦታ ፤ በሥራ ቦታው ፤ በሚማርበት ቦታ ወይም በእነዚህ ሁሉ አቅራቢያ፤ እንዲሁም ግብይቱ በገበያ ማዕከሎች ፤ በማዕከላዊ ጣቢያዎች ፤ ወ.ዘ.ተ. ከተካሄደ ነው:: የዝውውር ግብይት የተፈፀመ ከሆነ ሸማቹ ምርቱን ከተቀበለበት ቀን ጀምሮ እስከ 14 ቀናት ድረስ ወይም ሙሉ ዝርዝር መረጃውን በጽሁፍ ከተቀበለበት ቀን ጀምሮ ለነጋዴው ማስታወቂያ በመስጠት በማንኛውም ምክንያት ግብይቱን የመሰረዝ መብት አለው። ይህም ከሁለት ምርጫዎች ውስጥ የዘገየውን ምርጫ በመምረጥ ይሆናል። የተደረገው ግብይት አገልግሎትን የሚያበረክት ከሆነ ፤ ሸማቹ ስምምነቱ ከተፈፀመበት ቀን ጀምሮ ባሉት 14 ቀናት ውስጥ ወይም በስምምነቱ የተመለከቱትን ሁሉንም ዝርዝሮች በጽሁፍ ከተቀበለበት ቀን ጀምሮ ማንኛውንም ግብይቱን ቢሆን መሰረዝ ይችላል ። የሽያጭ ግብይት ከተሰረዘ ሸማቹ የስረዛ ክፍያ አይከፍልም። የተሸጠው የአገልግሎት አቅርቦት ቀጣይነት ያለው ግብይት ከሆነ ሸማቹ የአገልግሎቱ አቅርቦት ቢጀመርም በተቀጠረው የጊዜ ገደብ ውስጥ ግብይቱን መሰረዝ ይችላል ። በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች ሸማቹ በአገልግሎቱ የተጠቀመበትን አንጻራዊ ጥቅም ይከፍላል :: እንዲሁም ሻጩ አገልግሎቱን ለመስጠት በተጠቃሚው ቤት ልዩ መሳሪያዎችን ከተከለ (ለምሳሌ የመቀየሪያ ሳጥን ፤ ሳቴላይትና የመሳሰሉትን) ገዥው ለእነዚህ ዕቃዎች መጠቀሚያ የሚሆን የ 100 ሸቄል ክፍያ መክፈል አለበት ።
አካል ጉዳተኛ ፤ አረጋዊ ዜጋ ወይም አዲስ ገቢዎችን በተመለከተ የተሰጡ ልዩ መመሪያዎች
ሕጉ አካል ጉዳተኛ (የአካል ጉዳተኞች መብትን በተመለከተ በወጣው ሕግ መሠረት) 65 ዓመት የሞላው ሰው ወይም የአዲስ ገቢ የምስክር ወረቀት ከተቀበለበት ቀን ጀምሮ አምስት ዓመት ያላለፈ ሰው ወይም ከአዲስ ገቢዎች ማስተናገጃ ሚኒስቴር እንደ አዲስ ገብ ፈቅድ ያለው ፣ ያካሄደውን የሽያጭ ግብይቱን ወይም የእርቀት ሽያጭ ግብይቱ ስምምነት ከተፈጸመበት ቀን ጀምሮ በ 4 ወራት ውስጥ የመሰረዝ መብት ይኖረዋል ፤ ወይም ንብረቱን ከተረከበበት ቀን ወይም የገዛቸውን ቁሳቁሶች ግብይት ካደረገ ፤ ወይም ግብይቱ እርቀት ሽያጭ የተካሄደ ከሆነ ፤ ከእነዚህ ምርጫዎች የዘገየውን በመምረጥ ።የእርቀት ሽያጭ ግብይትን በተመለከተ ፤ እነዚህ መመሪያዎች ተግባር ላይ የሚውሉት በገዥውና በሻጩ መካከል የስልክ ግንኙነት ተደርጎ ከተወያዩ በኋላ ብቻ ነው ። በኤሌክትሮኒክስ ግንኙነት የሚደረግ ውይይትም ይህንን ሁኔታ ያሟላል ።
በእነዚህ መመሪያዎች መሰረት ግብይቱን ለመሰረዝ አከፋፋዩ ሸማቹ አካል ጉዳተኛ ፤ አዛውንት ወይም አዲስ ገቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እንዲያቀርብ ሊጠይቅ ይችላል ። ለአካል ጉዳተኛ ሸማቹ ከእነዚህ ሰነዶች ውስጥ አንዱን ማቅረብ አለበት፡-
ሸማቹ የምስክር ወረቀቶቹን በኤሌክትሮኒክስ ግንኙነት ማድረጊያ ዘዴዎች ወይም በፋክስ ማስተላለፍ ይችላል ።
በዕረፍት ክፍሎችና በስፖርት መስሪያዎች ውስጥ ለተወሰነ ጊዜ የሚደረጉ ግብይቶችን በተመለከተ የተሰጡ ልዩ መመሪያዎች
ለተወሰነ ጊዜ የሚደረግ ግብይት ማለት ሸማቹ ለተወሰነ ጊዜ የሚቆይ አገልግሎትን የሚገዛበት ግብይት ነው
- ለምሳሌ፣ የዕረፍት ጊዜ ማሳለፊያ ክፍል ወይም የመዋኛ ገንዳ ወይም የስፖርት መስሪያ ክፍሎች የሚደረጉ ስምምነቶች ፤ እንደዚህ ዓይነት ግብይቶችን መሰረዝ የሚቻለው ከተሰጡት መደበኛ መሰረዣ ደንቦችን በመከተል መሰረዝ ይቻላል ። ለምሳሌ፣ ሸማቹ ስምምነቱን ፈርሞ መጠቀም ከጀመረና ምዝገባውን ከጊዜው ቀደም ብሎ ለመሰረዝ ከፈለገ ሕጉ ይህን በተመለከተ የተለዩ መመሪያዎችን አስቀምጧል ።
የዕረፍት ክፍሎች
የዕረፍት ጊዜ ክፍል ማለት አንድ ሸማች አንድ ክፍል ወይም ሌላ የመኖሪያ ቦታ ቢያንስ ለሦስት ዓመታት ወይም ቢያንስ በዓመት ለሁለት ቀናት ለመጠቀም የገዛው መብት ነው ።
ይህን ዓይነቱን ግብይት ለመሰረዝ ሸማቹ ለነጋዴው የጽሁፍ ፤ በፖስታ ፤ ኢሜልን ፤ የኢሜል ፋክስን በመጠቀም ማሳሰቢያ መስጠት አለበት ።
የተሰረዘበት ጊዜ የሚፀናበት ቀን ማስታዎቂያዉን ወደ ማስረከቡ ሲቃረብና ሸማቹ የዕረፍት ጊዜ ክፍሉን የመጠቀም መብቱ ወደ መጨረሻው ላይ ሲደርስ ነው ። በዓመታዊ የአጠቃቀም ጊዜ የተሰጠ ማስታወቂያ ውሉ በዓመታዊው ቀን መጨረሻ ላይ እንዲሰረዝ ያደርጋል ።
ለዕረፍት ክፍል ግዢ የሚደረግ ግብይት ከተሰረዘ ሻጩ ከተጠቃሚው ሊቀበላቸው የሚችላቸው ብቸኛው ክፍያዎች ፤
ይህ የገንዘብ ክፍያ መከናወን የሚችለው ሻጩ ገዥውን በዕረፍት ክፍል ውስጥ ያሉትን የመሸጥ መብቶች እንደማይገድብ ካሳወቀ በኋላ ብቻ ነው ።
ሻጩ የውል ስረዛ ክፍያዎችን መቀበል አይፈቀድለትም እና ከላይ በአንቀጽ 1 እና 2 መሠረት መሰብሰብ ከተፈቀደለት መጠን ተቀንሶ የከፈለውን ማንኛውንም መጠን ለገዥው ይመለሳል ፣የተለያዩ ወለዶችንም ጨምሮ ።
የስፖርት መስሪያ ክለቦች
ስፖርት እንቅስቃሴ ማድረግ ማለት ማንኛውም ቦታ ጡንቻዎችን የሚያነቃቁ መሳሪያዎችን የሚያሰለጥኑበት ክለቦች ፤ የጤና እንክብካቤ የሚያበረክቱ ክበቦች ፤ የመዋኛ ገንዳዎች ፤ የጂምናስቲክ እና የሰውነት ቅርፅ መጠበቂያ ልምምዶች ፣ ሳውና እና ጃኩዚንም ያጠቃልላሉ ።
የስፖርት መስሪያ ክበቡ ውስጥ በመመዝገብ መቀላቀል የምትችለውና በኋላ ላይ መቀላቀል የምትችለውን በጥናት ፕሮግራም ላይ የተመሰረተ ክፍልን አያካትትም ። ስለዚህ በዓመት እስከ አምስት ወር ድረስ የሜሠራ የመዋኛ ገንዳ አገልግሎቶች ብቻ የሚሰጡበትን ቦታ አያካትትም ።
በስፖርት መስሪያው ክበብ ውስጥ ከተመዘገቡ በኋላ ለተወሰነ ጊዜ ውልን ለመሰረዝ ፤ የስረዛ ማስታወቂያ መላክ አለብህ ። ማስታወቂያው በጽሁፍ ፤ ፖስታ ፤ በኢሜል ወይም ፋክስ መላክ አለበት ። ስረዛው የስረዛ ማስታወቂያው ከተላከበት ቀን ጀምሮ ከአንድ ወር በኋላ ተግባራዊ ይሆናል።
ሻጩ የግብይቱን መሰረዝ ተከትሎ ክፍያዎችን ሊቀበል የሚችለው በግብይቱ አፈጻጸም ላይ በትክክል ከተተገበረ ብቻ ነው ። በዚህ ሁኔታ ክምችቱ እስከሚሰረዝበት ቀን ድረስ የመጠቀም መብትን ተመጣጣኝ ክፍል ለመክፈል ብቻ የተገደበ ነው ። አከፋፋዩ የስረዛ ክፍያ ሊያስከፍለው የሚችለው ከግብይቱ በፊት አከፋፋዩ ለሸማቹ የውል ሰነድ ባቀረበ ጊዜ ላልተወሰነ ጊዜ የግብይቱን ወርሃዊ ዋጋ ዘርዝሮ ባቀረበ ጊዜ ነው ።
የስረዛ ክፍያው ከታች ካሉት ሶስት አማራጮች ውስጥ በዝቅተኛው መጠን ይሰላል
የተደረጉ ግብይቶችን የመሰረዣ መንገዶች
ሻጩ ለሸማቹ ያለውን የመሰረዝ መብት ሥራ ላይ እንዲያውል መፍቀድ አለበት (ለተጠቃሚዎች ጥበቃ በተደነገገው ሕግ መሰረት ወይም በስምምነት) ፖስታ ፤ በኢሜል ፤ በፋክስ ፤ በእነዚህ መንገዶች መልክቱ ከደረሰው ውሉን እንዲሰርዝ መፍቀድ አለበት ። በኢንተርኔት አማካኝነት የተደረጉ ግብይቶች ከሆኑ ደግሞ ሻጩ በድረ- ገጹ ላይ ተለይቶ የሚታወቅ እና በግልጽ የሚቀመጥ የመገናኛ መስመር በማስቀመጥ ሸማቹ የሚያስፈልገውን መልእክት እንዲልክ ሁኔታዎችን ማመቻቸት አለበት ።
በማንኛውም ሁኔታ የስረዛ ማስታወቂያው በጽሁፍ መሆን አለበት ተብሎ በተወሰነበት ቦታ ላይ - ሸማቹ በቃል በመናገር ፤ በስልክ ወይም በማስታወቂያ በማሳወቅ ግብይቱን የመሰረዝ መብት ይኖረዋል ።
ሸማቹ በስረዛው ማስታወቂያ ውስጥ ስሙንና የመታወቂያ ቁጥሩን ፤ በቃላት ስረዛ ጊዜ - ከሻጩ ጋር ስምምነት የተደረሰባቸው ተጨማሪ የመታወቂያ መረጃዎችን መስጠት አለበት ።
ለመሰረዝ በቃል መልዕክት ብቻ መተማመን አያስፈልግም ፤ ከዚህ በተጨማሪ በሕጉ መሰረት በሚቻሉት መንገዶች በአንዱ የጽሁፍ መልዕክት ይላኩ ፤ የስረዛውን መልዕክት ጽፈው በመያዝ የሻጩን መልስ መከታተል ያስፈልጋል ።
በዚህ የመምሪያ መጽሔት ውስጥ የቀረበው መረጃ አጠቃላይ መረጃ ብቻ ነው ፤ ግን ሕጋዊ ምክርን የሚተካ አይደለም እና ያለ ተገቢ ምክር ብቻዉን መታመን የለበትም.
ይህ መምሪያ ሰኔ ወር 2023 ዓ.ም. ያለውን መረጃ በሕጉ እና ደንቡ ላይ በመመርኮዝ ተሻሽሏል ።
አስገዳጅ የሚሆነው የሕጉ እና የደንቡ ጽሑፍ ነው።