መድሎዎችን መከላከል
የመድልዎ ክልከላን የሚመለከተው ዋናው ሕግ በምርቶች ፤ አገልግሎቶች ፤ ወደ መዝናኛ ቦታዎች እና የሕዝብ መናሃሪያ ቦታዎች መግባትንና የመሳሰሉ ክልከላዎችን የሚያግድ ሕግ ነው ፤ በ 2000 ዓ.ም. :: የሕጉ ዓላማ እኩልነትን ለማስፈን ወይም ለማረጋገጥ እና ሕዝብ በሚሰበሰብበት ቦታ በመግባት ምርቶችን እና አገልግሎቶችን በማቅረብ መድሎዎችን ለመከላከል የተደነገገ ሕግ ነው ።
ለሰፊው ሕዝብ የሚሰጡ አገልግሎቶችን መግለጽ
ሕጉ የሕዝብ አገልግሎቶች የትራንስፖርት አገልግሎቶች (አውቶቡሶች ፤ ባቡሮች ፤ የአየር በረራዎችን ፤ መርከቦች፤ ማመላለሻ እና የመኪና ኪራይ አገልግሎቶች) ፣ ኮሙኒኬሽን ፤ ኢነርጂ ፣ ትምህርት ፤ ባህል ፤ መዝናኛ ፤ ቱሪዝም እና የፋይናንስ አገልግሎቶች (ባንክ ፤ ብድር እና ኢንሹራንስ) ናቸው ይላል ። ያልተገደበ የሕዝብ አጠቃቀም ማለት ነው።.
የሕዝብ መናሃሪያ ቦታን መሰየም
በሕጉ መሰረት ፣ የሕዝብ መናሃሪያ ቦታ ማለት ለሕዝብ ጥቅም ተብሎ የተደራጀ ማንኛውም ቦታ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ የጉብኝት ቦታ ፤ ሆቴል ፤ ሆስቴል ፤ የእንግዳ ማረፊያ ፤ የሕዝብ መሰባሰቢያ ቦታዎች ፤ የመጻሕፍት ቤቶች ፤ የቡና ቤቶች ፤ ለመዝናኛና ለባህላዊ ትርዒቶች አዳራሾች ፤ ሙዚየም ፤ ቤተ መጻሕፍት፤ የመዳነሻ ቦታዎች ፤ የስፖርት አዳራሽን ጨምሮ ፤ የመዋኛ ገንዳ ፤ የገበያ አዳራሽ ፤ ሱቅ ፤ ጋራዝ እንዲሁም የሕዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት አገልግሎቶችን ሁሉ ያጠቃልላል ።
ማን ነው የሚከለከለው? ኃላፊነቱስ ከማን ላይ ነው ?
የማድላት ክልከላ እና የተከለከሉ መድሎዎች ኋላፊነት የሚጣለው በሕዝብ ምርት ወይም አገልግሎት አቅርቦት ላይ በተሰማሩ ወይም በሕዝብ አገልግሎት ሥራ ላይ በተሰማሩት ግለሰቦች ላይ ነው። የአንድ የንግድ ድርጅት ባለቤት ፣ ሥራ አሥኪያጅ ወይም ሸቀጣ ሸቀጡን የሚያቀርበው ኃላፊ ወይም ለሕዝብ ምርት ወይም አገልግሎት የሚያቀርብ ወይም ለሕዝብ ቦታ በኋላፊነት የሚያሠራ ወይም የመግቢያ ፈቃድ የሚሰጥ ናቸው ።
የተከለከሉ መድሎዎች ማለት ምን ማለት ነው ?
የመድልዎ ክልከላው በዘር፤ በቀለም በሃይማኖት ወይም በሃይማኖት ቡድን ፤ በዜግነት ፤ በትውልድ አገር ፤ በፆታ ፤ በፆታ ዝንባሌ ፤ በአመለካከት ፤ በፓርቲ አባልነት ፤ በመኖሪያ ቦታ ፤ በዕድሜ ምክንያት ወደ ሕዝባዊ ቦታ ለመግባት ወይም አገልግሎት ለመስጠት የሚደረገውን መድሎዎችን ይመለከታል። ፣ የግል አቋም ፣ የወላጅነት ወይም የደህንነት ኋይሎችን ዩኒፎርም በመልበስ እና ምልክቶቻቸውን በማስቀመጥ ወይም በመልበስ ጥቅም ላይ ማዋል ፤ እነዚህ አካላት የመከላከያ ሰራዊት ፤ ፖሊስ ፤ የእስር ቤት አገልግሎት ፤ ማጌን ዴቪድ አዶም ፤ የእሳት አደጋ መከላከያ ባለስልጣን እና ማንኛውም አካል በብሔራዊ - ሲቪል ሰርቪስ ሕግ መሰረት ከጾታ ጋር ያልተያያዙ ሁኔታዎችን በማስቀመጥ መድልዎ የተከለከለ እንደሆነ ይገልፃል።
የማይካተቱ / የማይመለከታቸው
ምንም እንኳን ከላይ የተገለፀው ሕግ እንዳለ ሆኖ ፤ በሚከተሉት ሁኔታዎች ውስጥ የሚደረግ መድሎዎች ልክ እንደ ተከለከሉ መድልዎ እንደማይቆጠር ሕጉ ይናገራል ።
መሆኑም፣ በመኖሪያ ቦታ ምክንያት የሚደርሰውን መድልዎ በተመለከተ፣ የከተማዋ አስተዳደር በሚያደርገው ምርጫ ውስጥ ይህ ሕግ ሥራ ላይ አይውልም ፤ ይህም መሆን የሚችለው ሕጉ የደነገገውን ተመርኩዞ መሆን አለበት ።
በዚህ የመምሪያ መጽሔት ውስጥ የቀረበው መረጃ አጠቃላይ መረጃ ብቻ ነው ፤ ግን ሕጋዊ ምክርን የሚተካ አይደለም እና ያለ ተገቢ ምክር ብቻዉን መታመን የለበትም.
ይህ መምሪያ ሰኔ ወር 2023 ዓ.ም. ያለውን መረጃ በሕጉ እና ደንቡ ላይ በመመርኮዝ ተሻሽሏል ።
አስገዳጅ የሚሆነው የሕጉ እና የደንቡ ጽሑፍ ነው።