የዋጋ ቁጥጥር

የዋጋ ቁጥጥር

አከፋፋዮች የምርቱን ፍላጎት አላግባብ የሚጠቀሙበት ፤ ዋጋን የሚዘርፉበትና ምክንያታዊ ያልሆነ ትርፍ የሚያገኙበት ሁኔታ እንዳይፈጠር፣ በአስፈላጊነት የተገለጹ እና ዋጋቸው በህግ ("በመንግስት ቁጥጥር ስር ያሉ ምርቶች")ቁጥጥር ስር የሆኑ ምርቶችና አገልግሎቶች አሉ ።የእነዚህን ምርቶች ዋጋም የመቆጣጠር ሥልጣንና ኃላፊነት ያለው ሚኒስቴር -አለ። ዋጋቸው ቁጥጥር ከተደረገባቸው ምርቶች መካከልም ዳቦ፣ ወተት፣ እንቁላል ወ.ዘ.ተ ይገኛሉ።

አንዳንድ ጊዜ በልዩ ሁኔታዎች ምክንያት አስፈላጊ ናቸው የተባሉት ምርቶች ዋጋዎች ለተወሰነ ጊዜ ቁጥጥር ይደረግባቸዋል ። ለምሳሌ ፤ በመጀመርያው የባህረ ሰላጤ ጦርነት ወቅት፣ ከጋዝ ኬሚካል የጦር መሳሪያዎች ለመከላከል ፣የመደበቂያ ክፍሎችን በልዩ ተለጣፊ ወረቀት ለመድፈን የሚያገለግል ወረቀት ላይ የዋጋ ቁጥጥር ተደርጎበት - ነበር ።

በመንግሥት ቁጥጥር ስር ያሉ ምርቶች ላይ ማስታወቂያ የመለጠፍ ግዴታዎች አለባቸው ።

አንድ አከፋፋይ በሱቁ ውስጥ በምርቱ አጠገብ በክትትል ወይም በቁጥጥር ስር ያሉትን ምርቶች እና ዋጋቸውን የሚገልጽ ምልክት ማስቀመጥ አለበት:: በተመሳሳይ ግዴታ በሩቅ የሽያጭ ግብይት ላይ በአከፋፋዩ የተገለጸው (ከዚህ በታች ያለውን መግለጫ ይመልከቱ:: የእርቀት ሽያጭ ግብይት) ፤ እንዲሁም ቁጥጥር የሚደረግበት ምርት አምራች፣ የምርት ዋጋ በመንግሥት ቁጥጥር ስር መሆኑን የሚገልጽ ጽሁፍ በምርቱ ማሸጊያ ላይ መታተም አለበት ።

 

 

 

המידע המובא במדריך זה הוא מידע כללי בלבד, הוא אינו תחליף לייעוץ משפטי ואין להסתמך עליו ללא ייעוץ מתאים.

המידע במדריך מעודכן בהתאם להוראות החוק והתקנות עד לחודש יוני 2023.

הנוסח המחייב הוא נוסח החוק והתקנות.