ዋጋዎችን የማሳወቅ ግዴታ
በሕጉ መሰረት ፤ በአገሪቱ ውስጥ በተመረቱ ምርቶች ላይ ያለው ምልክት በዕብራይስጥ ቋንቋ መሆን አለበት ፤ ከአገር ውጭ የሚገቡ ምርቶችም በዕብራይስጥ ምልክት መደረግ አለባቸው ። ምልክት ማድረጊያው ግልጽ እና ሊነበብ የሚችል እና ከሌሎች ነገሮች በተጨማሪ የምርት ስም እና የንግድ ስሙ ፤ የአምራች ስም እና አድራሻ ፤ ምርቱ ከመጣ - የአስመጪው አድራሻ እና የአምራች አገር ስም መካተት አለበት ።
ምርቱ ከታደሰ፣ ከተበላሸ ወይም ከኦርጅናል ምርቶች የሚመደብ ዓይነት ከሆነ ፣ይህ ምልክት በምርቱ ላይ መጠቀስ አለበት ። እንዲሁም ዋጋቸው በመንግሥት ቁጥጥር ስር የሆኑ የምግብ ምርቶችን በተመለከተ ከፍተኛ ዋጋቸው እና እንዲሁም ዋጋው ቁጥጥር ስር ያለ መሆኑ መገለጽ አለበት።
ዋጋዎችን የማሳየት ግዴታ
ዋጋዎቹን የማሳየት ግዴታ በነጋዴዎች ላይ ከተጣሉት ዋና ዋና ግዴታዎች አንዱ ነው ። በሕጉ መሰረት አከፋፋዩ ዋጋውን ግልጽ በሆነና በሚታይ ቦታ፣ በደንብ በሚነበብ ጽሑፍ ማሳየት አለበት ። ዋጋው በእስራኤል የገንዘብ ስያሜ መጠቀስ አለበት፣ ስለዚህ ዋጋዎች በውጭ ምንዛሬዎች ማስታወቂያ አይደረጉም፣ (ምክንያቱም ሸማቹ ዝቅተኛ ዋጋ እየከፈልሁ ነው ብሎ ሊያስብ ስለሚችል ነው) ። ከእስራኤል ውጭ ሊደረግ የታሰበ አገልግሎት ወይም ከእስራኤል ውጭ የሚሸጥ ንብረት ከሆነ፣ አከፋፋዩ ዋጋውን በውጭ ምንዛሪ ማተም ይችላል ። የሚታየው ዋጋ ደግሞ ሸማቹች የሚከፍሉት የመጨረሻ ዋጋ መሆን አለበት ፤ ማለትም፤ ማንኛውም ታክስ ለሽያጭ የቀረቡ እና በማድረስ ለሚቀርቡ ምርቶች ፤ የሚታየው
ዋጋ የመላኪያ ክፍያዎችን ማካተት አለበት ። እነዚህ በሸማቹ ኋላፊነት ላይ የተጣሉ ናቸው:: እና እነሱን ማስቀረት አይችልም ፤ ይህም ከሸማቹ ተጨማሪ ዋጋ ማለትም እንደ የደህንነት ክፍያ ወይም የአገልግሎት ሰጭ ድጎማ ("ቲፕ") መጠየቅ የተከለከለ ነው.
በዋጋ ዝርዝሩ ላይ ከተገለጸው በላይ፣ ከማስታወቂያው ላይ የተወሰነው ዋጋ ሸማቹች የሚከፍሉት የመጨረሻ ዋጋ ነው ተብሏል ። ማንኛውም ተጨማሪ የአገልግሎት ድጎማ መስጠት ከወሰነ ብቻ መስጠት ይችላል ።
የአንድ መለኪያ ዋጋ
በጅምላ ወይም ታሸገው የተሸጡ ሸቀጦችን በተመለከተ ፤ በሕጉ ላይ በተጠቀሰው መስፈርት መሰረት ብዛታቸው መጠቀስ አለባቸው ፤ የእያንዳንዱ መለኪያ ዋጋ መታየት አለበት ። በአንድ መለኪያ ዋጋ ለ 1 ኪሎ ግራም ምርት ፤ 1 ሊትር ምርት ፤ የምርት 1 ሜትር ፤ የምርት 1 ካሬ ሜትር ፤ 100 ግራም ምርት ወይም 100 ሚሊ ሊትር አጠቃላይ ዋጋ ነው ፤ ለምሳሌ ፤ ምርቱ በ 15 ኪሎ ግራም ታሽጎ የተዘጋጀ ከሆነ የጠቅላላው ምርት ዋጋ ተተምኖ መታየት አለበት፣ ከዚህ ዋጋ ጎን ለጎንም የ- 1 ኪሎ ግራም ምርቱ ዋጋ መታየት አለበት ። አንዳንድ ምርቶች በሕጉ መሰረት የተለዩ ናቸው ተብለው ስለተወሰኑ፣ የዋጋ ምልክት ማሳየት ግዴታ የለባቸውም ፤ ለምሳሌ ፤ በጅምላ የሚሸጡ የምግብ ምርቶች ፤ ያልታሸጉ ምርቶችና በትልልቅ ጋኖች ውስጥ ሆነው የሚሸጡ ምርቶች ወ.ዘ.ተ.።
በኢንተርኔት ድረ - ገጽ አማካኝነት ዋጋዎችን የማስታወቅ ግዴታ
ሕጉ ትልቅ ቸርቻሪ የሆነ አከፋፋይ (እንደ ትልቅ የምግብ ሰንሰለት ያሉ) የምርቶቹን ዋጋ በሱቆቹ ውስጥ በኢንተርኔት ላይ እንዲያትም ያስገድዳል። ዋጋዎቹ በነጋዴው ድረ-ገጽ ላይ እና በሸማቾች ጥበቃና ፍትሃዊ ንግድ ባለስልጣን ድረ-ገጽ ላይ መታተም ያለባቸውን ህትመቶች፣ ህብረተሰቡ አውርዶ በመመዝገብ ፋይሎች እንዲጠብቃቸው ነው። አከፋፋዩ የሁሉንም መደብሮች አድራሻዎች እና ዝርዝሮች እንዲሁም ተጨማሪ ፋይሎችን ለእያንዳንዱ መደብር አንድ ፋይል የማተም ግዴታ አለበት ፤ በዚህ ሱቅ ውስጥ ያሉ ምርቶች ዋጋዎች እውቅና አግኝተዋል ። ፋይሉ ስለ ምርቶቹ ባህሪ ፤ በክምችት ውስጥ ስላላቸው መጠን ፤ ዋጋቸው ፤ የአምራቹና የአስመጭው ማንነት ፤ ልዩ የዋጋ ቅናሽ ሽያጮችን እና ከመደበሩ ውስጥ ስላሉት ምርቶች ብዛት ዝርዝር ከአንድ ቀን ቀደም ብሎ ማስተካከል ያስፈልጋል።ያሉት ምርቶችና ዋጋቸው ቢያንስ ቢያንስ ከአንድ ሰዓት ቀድም ብሎ መስተካከል አለባቸው ።
በሸማቾች ጥበቃ ሕግ መሰረት፣ ትላልቅ የግብይት ገበያ ቦታዎች ለተጠቃሚዎች አገልግሎት የሚውል የኤሌክትሮኒክስ መለኪያ መሣሪያ ማስቀመጥ አለባቸው ። የመለኪያ መሳሪያው ከክፍያ በፊት ክብደት መለካት የሚያስፈልጋቸውን ምርቶች አቅራቢያ በሆነ ቦታና በሚታይ ቦታ ይቀመጣል ። በዚህ መንገድ ሸማቹ ወደ ክፍያ ቦታው ከመድረሱ በፊት ለመግዛት የሚፈልገውን ምርት ክብደት ምን ያህል መሆኑን ማወቅ ይችላል ። ድንጋጌው የሚመለከተው ከ 300 ካሬ ሜትር በላይ ስፋት ያላቸው የትላልቅ የግብይይት ቦታዎች (በዓመት 250 ሚሊዮን ሸቄል ገቢ ያለው ወይም ከዚያ በላይ የሆነ የግብይት ቦታን ይመለከታል) ።
የተገዛ ምርትን የመመለሻ ፖሊሲን ማስታዎቅ
ማንኛውም ሻጭ በማስታወቂያው ላይ በግልፅ ፤ በሚነበብ መልኩ እና በሚታይ ቦታ ላይ የተገዙ ሸቀጦችን የመመለስ ፖሊሲውን ማስቀመጥ አለበት ። ሸማቹ በጉድለት ምክንያት ያልሆነውን ምርት እንዲመልስ ከጠየቀ እና ፣አከፋፋዩ ያስታዎቂውን ፖሊሲ ለመፈጸም ፈቃደኛ ካልሆነ፣ ሸማቹ በአንድ ሳምንት ውስጥ ምርቱን መመለስ እና ገንዘቡን መቀበል ይችላል ። የመመለሻ ፖሊሲውን የሚገልጽ ማስታወቂያ ጨርሶ ካልታየ ፤ በሕጉ መሠረት አከፋፋዩ ጥቅም ላይ የማይውሉ ምርቶችን እንዲመለስ እንደፈቀደ ይቆጠራል ። ምርቶቹን የመመለስ መብት የሚኖረው የምርቱ ሁኔታ ካልተበላሸ ብቻ መሆኑን ልብ ሊባል የሚገባው ጉዳይ ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ ፤ ሸቀጡ የታሸገበትን መክፈት ምርቱን ማበላሸት ተደርጎ እንደማይታይ መታዎቅ አለበት ።
ስምምነቱን እና ከስምምነት ጋር የተያያዙ ሌሎች ሰነዶችን የመገምገም መብት
አንድ ሸማች ከአከፋፋይ ጋር ውል ሊፈራረም ሲል አከፋፋይ ውሉን ከመፈረሙ በፊት ሸማቹ እንዲመረምር መፍቀድ አለበት ። ከተፈረመ በኋላ አከፋፋይ ለተጠቃሚው የስምምነቱን ቅጂ መስጠት አለበት ። የዋስትና ደብዳቤ የተሰጠበትን ምርት ወይም አገልግሎት ሲገዙ፣ ሸማቹ ከመግዛቱ በፊት የዋስትና ደብዳቤውን የማየት መብት አለው ። ሻጩ በሚገዛበት ጊዜ ለሸማቹ የዋስትና የምስክር ወረቀት ቅጂ መስጠት አለበት ።
ሰነዶችን ይፋ ማድረግ
ሕጉ በወሰነው መሰረት ፣ በልዩ ግብይቶች ውስጥ (እንደ መሸጫ ግብይት እና የርቀት ሽያጭ ግብይት ፤ በቀጣይ የምንመለከተው ይሆናል) በሕግ በተደነገገው መሠረት ፤ ነጋዴው የግብይቱን ዝርዝርና የተገልጋዩን የመሰረዝ መብትን በሚመለከት ዝርዝር መረጃ የያዘ የጽሁፍ ሰነድ ለሸማቹ ማቅረብ አለበት ይላል ።
የየምርቶች አጠቃቀም መመሪያዎች
በዕብራይስጥ ቋንቋ ጥቅም ላይ የሚውሉ መመሪያዎች ጋር መያያዝ ያለባቸው የምርቶች ዝርዝር አለ ። በዚህ ዝርዝር ውስጥ በተካተተው ወደ ሀገር ውስጥ በገባ ምርት ውስጥ ምርቱን ለመጠቀም መመሪያው እንዲሁም በላዩ ላይ የሚታዩ ማስጠንቀቂያዎች ወደ ዕብራይስጥ ቋንቋ መተርጎም አለባቸው። በውጪ ቋንቋ የተጻፉ የአጠቃቀም መመሪያዎችን በትክክኛ መልኩ መተርጎም አለባቸው ።
በዚህ የመምሪያ መጽሔት ውስጥ የቀረበው መረጃ አጠቃላይ መረጃ ብቻ ነው ፤ ግን ሕጋዊ ምክርን የሚተካ አይደለም እና ያለ ተገቢ ምክር ብቻዉን መታመን የለበትም.
ይህ መምሪያ ሰኔ ወር 2023 ዓ.ም. ያለውን መረጃ በሕጉ እና ደንቡ ላይ በመመርኮዝ ተሻሽሏል ።
አስገዳጅ የሚሆነው የሕጉ እና የደንቡ ጽሑፍ ነው።