የተለያዩ የግብይይት ማስታወቄያዎች ፤ ከተለያዩ ስብስቦች የተወሰደ "አትደውሉልኝ"

የተለያዩ የግብይይት ማስታወቄያዎች ፤ ከተለያዩ ስብስቦች የተወሰደ "አትደውሉልኝ"

 

ለሸማቾች መብት ጥበቃ ሲባል የተደነገገው ሕግ እንደወሰነው ከሆነ ፤ የፍትሃዊ ንግድ ድርጅት የተለያዩ የግብይት ጥያቄን አለመቀበል ለሚፈልጉ ደንበኞች የስልክ ቁጥራቸውን በመመዝገብ ማንኛውንም የንግድ ጥሪ አንዳይቀበሉ መዝገብ ማዘጋጀት አለባቸው ፤ አንድ ሸማች የስልክ ቁጥሮቹን በመረጃ ደብተሮች ውስጥ ማጻፍ ይችላል ፤ ይህ ከሆነ ደግሞ ፤ አከፋፋዩ በእነዚህ ስልክ ቁጥሮች በመደወል ከገበያ ጥያቄ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን በተመለከተ እንዳያነጋግረው ይከለከላል።

ለዚሁ ዓላማ ፤ንግዱን በተመለከተ ለአንድ ደንበኛ በስልክ ማነጋገር ከዚህም በመጨመር ለሸማቹ ያለምንም ክፍያ ቤት ወይም የተለያዩ አገልግሎቶችን እሰጣለሁ ብሎ መናገር የተከለከለ ነው በስልክ ቁጥር

-መመዝገቢያ ውስጥ ባለው የደንበኛው ስልክ ቁጥር ተጠቅሞ ወደ ግለሰቡ መደወል ወይም ስልክ ቁጥሩ ከተጻፈበት ደብተር እንዲሰርዝ ተጸዕኖ ማድረግ የተከለከለ ነው

 

 

ምዝገባ የሚደረገው በኢንተርኔት የሸማቾች ጥበቃና ፍትሃዊ ንግድ ባለሥልጣን ድረ-ገጽ ነው።

ሕጉ እንደሚጠቅሰው ከሆነ የስልክ ቁጥር ማከማቻውን በመጠቀም ሻጩ ወደ ተጠቃሚው በስልክ እንዳይደውል እና ግንኙነት እንዳያደርግ ይከለከላል ።

  1. አንድ ሻጭ ወደ ደንበኛ ሸማቹ መደወል እና በስልክ ማነጋገር የሚችለው ደንበኛው ወደ ሻጩ ደውሉ በስልክ አገልግሎት እንዲቀበል ከፈቀደ ብቻ ይሆናል ። ሸማቾቹን ደውሎ አገልግሎቱን እንደጠየቀ ማስረጃ የማቅረቡ ኃላፊነት በሻጩ ላይ ብቻ ነው ።
  2. ለብዙ ጊዜ በሚካሄድ ግብይት (በአብዛኛው የጋዝ አቅርቦት ግብይትን ጨምሮ) ከሸማቹ ጋር የተዛመደ አከፋፋይ በግብይት ወቅት እና ግብይቱን በተመለከተ የግብይት ጥያቄን በመጠየቅ ሊያነጋግረው ይችላል፤ ይህም ውሎችን የመቀየር ችሎታን ይጨምራል ። ሆኖም ነጋዴው ያለውን ግብይት ትክክለኛነት ለማራዘም በእራሱ ተነሳሽነት በተፈቀደው ጥያቄ ካልሆነ በስተቀር፣ ሻጩ ሌላ ግብይትን በሚመለከት የግብይት ጥያቄን ወይም ያለውን ግብይት ማራዘምን በተመለከተ ሸማቹን ማነጋገር አይችልም ። የነባር ግብይቱን ትክክለኛነት ለማራዘም ሸማቹ በእራሱ ተነሳሽነት ለጠየቀው የማረጋገጥ ግዴታ በነጋዴው ላይ ነው።
  3. ሻጩ ወደ ሸማቹ ደውሎ ማስታዎቂያ ነክ ንግግሮችን ማነጋገር የሚችለው ግልጽ እና የተለየ ፈቃድ ከሰጠውና በዚህ ስምምነት መስማማቱን በስልክ ደውሎ ካረጋገጠ በኋላ ብቻ ነው ። ይህ ዓይነት ስምምነት በተለየ ደብዳቤ መጻፍ አለበት ። ይህ ስምምነትም በኤሌክትሮኒክስ ጨምሮ በተለየ የጽሑፍ ሰነድ ውስጥ ይሰጣል ። ለግብይት ጥያቄው ስምምነት በተጠቃሚው እና በአከፋፋዩ መካከል ያለውን ስምምነት እንደማይመለክት ግልጽ ይሆናል ፤ ተገልጋዩ ቀደም ብሎ ፈቃዱን ካልሰረዘ በስተቀር የተጻፈው ስምምነት ቢበዛ ለአንድ ዓመት የሚቆይ ይሆናል ። ከዚህ በላይ በተጠቀሰው መንገድ በተጠቃሚው ፈቃድ፤ በአንድ ጊዜ ቢበዛ ለአንድ ዓመት ሕጋዊነትን ማራዘም ይቻላል።
  4. ሸማቹ በእራሱ ተነሳሽነት ሻጩን ካነጋገረ እና ለእንደዚህ ዓይነት ጥያቄ ግልጽ ፍቃድ ከሰጠው ፣ ሻጭ ከግብይት ጥያቄ ጋር ተገልጋዩን ማነጋገር ይችላል። ፈቃዱ ለአንድ ዓመት የሚሠራ ይሆናል፣ ነገር ግን ሸማቹ በማንኛውም ጊዜ ፈቃዱን ማንሳት ይችላል። የተገልጋዩን ፈቃድ እና ተቀባይነትን በተመለከተ የማስረጃው ግዴታ በአከፋፋዩ ላይ ነው።

 

 

በዚህ የመምሪያ መጽሔት ውስጥ የቀረበው መረጃ አጠቃላይ መረጃ ብቻ ነው ፤ ግን ሕጋዊ ምክርን የሚተካ አይደለም እና ያለ ተገቢ ምክር ብቻዉን መታመን የለበትም.
ይህ መምሪያ ሰኔ ወር 2023 ዓ.ም. ያለውን መረጃ በሕጉ እና ደንቡ ላይ በመመርኮዝ ተሻሽሏል ።
አስገዳጅ የሚሆነው የሕጉ እና የደንቡ ጽሑፍ ነው።