አንድን ነጋዴ ከግብይቱ ጋር ለማያያዝ በሸማቹ ላይ የውል ነፃነቱን የሚነፍገው ወይም ባለማወቅ የሚደርሱትን መብቶች በተለያዩ መንገዶች የሚጎዳውን ኢ-ፍትሃዊ ተፅእኖ ማድረግ የተከለከለ ነው ።
የሸማቾችን መብት ጥበቃ ለማድረግ በተደነገገው ሕግ ላይ የተለያዩ ፍትሐዊ ያልሆኑ ተፅኖዎችን የሚያደርጉ ዝርዝር ሁኔታዎች ተቀምጠዋል፣ ከዚህ ጎን በጎንም ጠቅላላ ተፅኖ ማድረግ የተከለከለ መሆኑም አብሮ ተቀምጧል ።
ለምሳሌ፡- የአንድ ሸማች ግለሰብን ቦታ የመልቀቅ አቅሙን መገደብ ፤ መመካከርን መከልከል ፤ ለሸማቹ ወይም ለቤተሰቡ አባላት ተደጋጋሚ ጉብኝት በማድረግ ወይም ግንኙነት በመፈጠር ግለሰቡ ግብይቱን እንዲያደርግ
- ጫና መፍጠር ፤ ቋንቋ አለማወቅን በመመርኮዝ ተፅኖ ማድረግ ፤ የተገልጋዩን የአእምሮ በሽታዎች ወይም የአካል ጉድለት መጠቀሚያ ከማድረግ፤ ከግለሰቡ ላይ መዛት ወይም ግለሰቡን ማስፈራራት ፤ ክፍያ የሌለበት ቁሳቁስ ወይም አገልግሎት ማቅረብ ፤ ግለሰቡን ሽልማት በሌለበት ቦታ ላይ ልክ ሽልማት እንዳገኘ አድርጎ ማሳመንና፣ በሌላ ጎኑ ደግሞ ይህን ሽልማት ለመቀበል ክፍያ ያስፈልጋል ብሎ ከወዲሁ ሳያስታውቁ ግለሰቡ ላይ ተፅኖ ማድረግ ።
በዚህ የመምሪያ መጽሔት ውስጥ የቀረበው መረጃ አጠቃላይ መረጃ ብቻ ነው ፤ ግን ሕጋዊ ምክርን የሚተካ አይደለም እና ያለ ተገቢ ምክር ብቻዉን መታመን የለበትም.
ይህ መምሪያ ሰኔ ወር 2023 ዓ.ም. ያለውን መረጃ በሕጉ እና ደንቡ ላይ በመመርኮዝ ተሻሽሏል ።
አስገዳጅ የሚሆነው የሕጉ እና የደንቡ ጽሑፍ ነው።