የሠራተኞች አንድነት ድርጅት ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ የሸማቾችን ጥቅም ለማስከበር እየሠራ ይገኛል ። ይህም ማለት የሠራተኛው ገቢና የኑሮ ደረጃ እና የሚደርሱትን መብቶች ማስጠበቅ የማይነጣጠሉ አካሎች መሆናቸውን በመረዳት በሚያደርጋቸው የቁሳቁስ ጥቅሞች ላይ እንቅስቃሴውን ማጠንከር እንዳለበት ተመልክቷል ።
የሸማቾች አንድነት ድርጅት የተቋቋመው በ 1970 ፤ በመጀመሪያ በሠራተኞች አንድነት ድርጅት ውስጥ "የሸማቾችን ጥቅም አስከባሪ" ተብሎ ተሰየመ ። በ1983 ዓ.ም. አገሪቱ ይህን ድርጅት የሸማቾችን ጥቅም አስከባሪ ድርጅት በማለት ዕውቅና ሰጠችው ። በ 1984 ዓ.ም. የፍርድ ቤት ባወጣው ሕግ መሠረት ይህ ድርጅት የሸማቾች መብት አስከባሪ በመባል ይታወቃል ፤ በተጨማሪም ዕውቅና ያገኘባቸው ዓመቶች ፤ 1981 ዓ.ም. የኢኮኖሚ ውድድር ከዚህ በተጨማሪም በ 1953 ዓ.ም. የዚህ ድርጅት ተወካይ በቁሳቁስ ደረጃ ጥበቃ በሚከታተል ድርጅት ውስጥ የመሳተፍ መብት አንዲኖረው ተወስኗል ።
በዚህ ድርጅት ኃላፊ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሲኖረው፣ መ/ቤቱም በሠራተኞች አንድነት ድርጅት ውስጥ በቴል አቪቭ ይገኛል ። አብዛኛው ሥራ የሚሠራው በአገሪቱ ውስጥ ተስራጭተው በሚገኙ የሠራተኞች መብት አስከባሪ ሠራተኞች አማካኝነት ነው ፤ እነዚህ የሸማቾች መብት አስከባሪ ኃላፊ ሠራተኞች ብዙ የሙያ ልምዶችን ያካበቱ ሲሆነ፣ ሽመታን በተመለከተ የተለያዩ የትምህርት ልምምዶችን ሁልጊም ይማራሉ ።
የሸማቾች መብት አስከባሪ ድርጅት በየዓመቱ የተለያዩ አቤቱታዎችን በተመለከተ አስፈላጊውን ዕርዳታ ያበረክታል። ለምሳሌ ዕቃዎችን ፤ የመገናኛ አውታሮችን (የተንቀሳቃሽ ስልክ ድርጅቶችን ፤ ኢንተርኔት ፤ የሳቴላይት ቴሌቪዥኖች) ፤ በኤሌክትሪክ የሚሠሩ መሳሪያዎችን ፤ አልባሳትን ፤ ጫማዎችን የዕረፍት ጊዜ ማሳለፊያ ቦታዎችን ፤ የእስፖርት መስሪያ ቤቶችን ፤ የተለያዩ የትምህርት ኮርሶችን ፤ ተንቀሳቃሽ ስምምነቶችን (ከሸማቹ ቤት ወይም መንገድ ላይ) እና በእርቀት የሽያጭ ግብይቶች (በስልክ፣ በኢንተርኔት ወዘተ መግዛት)። የድርጅቱ ተወካይ ሠራተኞች በየጊዜው በተለያዩ የክኔሴት ኮሚቴዎች ቀርበው የሸማቾችን ሕግ ያብራራሉ ይመለከታሉ ። እነዚህ ተወካዮች የሸማቹን ፍላጎት የሚወክሉና ሕጉን ለተጠቃሚው የሚጠቅም መሆኑን ካረጋገጡ በኋላ ተግባራዊ እንዲሆን የሚያራምዱ ናቸው ። የድርጅቱ ባለሙያዎች እና በጎ ፈቃደኞች በእስራኤል የደረጃዎች መወሰኛ ኢንስቲትዩት ደረጃ አሰጣጥ ኮሚቴዎች ውስጥ መመዘኛዎችን በማውጣት የተጠቃሚውን ፍላጎት ይወክላሉ ። ከጊዜ ወደ ጊዜ የድርጅቱ ተወካዮች ከሸማቾች መብት ጥበቃ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን የሚመለከቱ የተለያዩ የሕዝብ ኮሚቴ አባላት ይሾማሉ ።