የግዢ ማስታወሻዎች

ሕጉ የግዢ ትዕዛዞችን በተመለከተ ልዩ ድንጋጌዎችን ያዘጋጃል፣ ከታች ያሉት ዝርዝሮች ዋናዎቹ ናቸው

የግዢ ትዕዛዝ ትክክለኛነት

  1. እያንዳንዱ የመግዣ ትዕዛዝ ቢያንስ ቢያንስ ለአምስት ዓመታት ያገለግላል
  2. የመግዣ ትዕዛዙን የሚሰጠው አካል የሚያልቅበትን ቀን ለመለወጥ ከፈለገ ፤ ይህን ማድረግ የሚችለው የመግዣው ትዕዛዝ አምስት ዓመት ካለፈው በኋላና ፈቃዱን የሚሰጠው አካል ስምና የወጣበት ቀን ጎላ ብሎ በዝርዝር ከተጻፈ ብቻ ነው ።
  3. በተጨማሪም ፤ ይህ የመግዣ ትዕዛዝ በማንኛውም የገብያ ቦታ ዋጋው 95% ወይም 90% ብቻ መከበር ያስፈልገዋል ብሎ መወሰን አይቻልም ፤ ማንኛውም የገብያ ቦታ ይህን የመግዣ ፈቃድ 100% ተግባር ላይ ማዋል አለባቸው ።

በመግዣ ትዕዛዝ ገዝተን መልስ ቢኖረን

አንድ ሸማች ለግዢ ከልክ ያለፈ ክፍያ ሲቀበል ፤ ሻጩ ተመልሶ የሚገዛበት የደረሰኝ ፈቃድ መስጠት እንጂ ጥሬ ገንዘብ ሊሰጠው አይችልም ፤ ጥሬ ገንዘብ መስጠት የሚችለው እነዚህ የመግዣ ትዕዛዝ ፈቃዶች ያላቸው የንግድ ምልክት አንድ ዓይነት ከሆነ ብቻ ይሆናል ።

በመግዣ ትዕዛዝ በመጠቀም የተገዛውን ምርት ስለመመለስ

የመግዣ ትዕዛዝ ፈቃድን ተጠቅሞ የተገዛ ምርት ከተመለሰ ፣ሻጩ በጥሬ ገንዘብ ከመመለስ ይልቅ ተመልሶ የመግዣ ትዕዛዝ ሊሰጥ ይችላል ፤ ይህ የሚሆነውም በመግዣ ትዕዛዝ አጠቃቀም ላይ ምንም ገደብ ከሌለ ብቻ ነው ፤ (በዚህ የመጠቀሚያ ካርድ ላይ ቀደም ሲል የነበረ ገደብ ካልሆነ በስተቀር) ።

የገንዘብ ማስመለሻ ካርድ ወይም ስጦታ

አንዳንድ ጊዜ ሻጩ ለሸማቹ የገዛውን ዕቃ የመመለስ መብት ያለው፣ ሁኔታዎች ካልተሟሉ የሸጨውን ዕቃዎችን ወይም አገልግሎቶችን ለመግዛት የተስማሙበትን ስምምነት ለመሰረዝ ይችላል ። አብዛኛውን ጊዜ ፤ እንደዚህ ባሉ አጋጣሚዎች ሻጩ ለተጠቃሚው የብድር መመለሻ ካርድ ይሰጣል ። ሕጉ በብድር መመለሻውና በስጦታው ካርድ ላይ የተጻፈው እንዳይሰረዝ በሚያግድ መንገድ መታተም ወይም መጻፍ አለበት ይላል ። በብድር መመለሻው ውስጥ የተገለው የገንዘብ መጠን በግብይቱ ወቅት የሚከፈለው መጠን ይሆናል ፤ የብድር መመለሻው ካርድ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ ለሁለት ዓመታት ያገለግላል ፤ የመግዣውን ካርድ በመጠቀም የክፍያ መጠየቂያ ደረሰኝ ጊዜ የተወሰነ አይሆንም ። በልዩ ሽያጭ ውስጥ የመግዣ ካርዶችን ጨምሮ ማንኛውንም ካርድ የማስመለስ ዕድልን የሚገድቡ ሁኔታዎች ተቀባይነት የላቸውም ።

ሕጉ በእነዚህ ክርዶች ላይ ገደቦችን የሚፈቅዱ ደንቦችን ጨምሮ እንዲያስገባ ይፈቅዳል ፤ ነገር ግን ይህ መመሪያ ከተጠናቀረበት ጊዜ ጀምሮ እንደዚህ ያሉ ደንቦች ገና ከካርዱ ውስጥ አልገቡም ነበር ።

 

 

 

በዚህ የመምሪያ መጽሔት ውስጥ የቀረበው መረጃ አጠቃላይ መረጃ ብቻ ነው ፤ ግን ሕጋዊ ምክርን የሚተካ አይደለም እና ያለ ተገቢ ምክር ብቻዉን መታመን የለበትም.
ይህ መምሪያ ሰኔ ወር 2023 ዓ.ም. ያለውን መረጃ በሕጉ እና ደንቡ ላይ በመመርኮዝ ተሻሽሏል ።
አስገዳጅ የሚሆነው የሕጉ እና የደንቡ ጽሑፍ ነው።