የመክፈያ ዘዴዎችን በአግባቡ መጠቀም

የመክፈያ ዘዴዎችን በአግባቡ መጠቀም

የክፍያ አገልግሎቶችን በተመለከተ የተደነገገው ሕግ መግቢያ

በ 2020 ዓ.ም. የተደነገገውን የክፍያ የአገልግሎቶች ሕግ ተደንግጎ ሥራ ላይ ውሏል ። በሥራ ላይ የዋለው አዲሱ ሕግ በኢንተርኔት ከክፍያ መተግበሪያዎች ጎን ለጎን ያሉ የክፍያ ዘዴዎች (ጥሬ ገንዘብ ፣ ቼኮችና የክሬዲት ካርዶች) አማካኝነት የሚደረጉ ክፍያዎች እየበዙ ስለመጡ፣ ካለእነሱ አስፈላጊውን አገልግሎት ለመስጠት ሲባል ነው ። የተራቀቁ የክፍያ ዘዴዎች ብዙ ጥቅሞች አሏቸው። ተጨማሪ የክፍያ አገልግሎት የሚያቀርቡ ድርጅቶች በመሳተፋቸው ያለውን የክፍያ ውድድር ይጨምረዋል ። የአገልግሎት ዋጋን በመቀነስና ለደንበኞች ምቹና ተደራሽነትን በማሻሻል ልዩ ሚና ይኖረዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ፤ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ዘዴዎችን መጠቀምም ጉዳቶች አሉት - ሰርጎ ገቦች / አጭበርባሪዎች የካርዱን መረጃዎች ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ በማሰባሰብ ከተጠቃሚ ደንበኞች ዝርዝር መረጃ ማውጣትና በመረጃው ለተለያዩ ሕገ ወጥ ለሆኑ ድርጊቶች ሊጠቀሙበት ይችላሉ ።

በእነዚህ ምክንያቶች የመክፈያ ካርዶችን በተመለከተ የተደነገገው ሕግ ቁጥር 8 19 በተስፋፉ ገብያዎች ላይ ሙሉ በሙሉ ምላሹን አይሰጥም። ስለዚህ የክፍያ አገልግሎት ሕግ ተደነገገ ይህ ሕግም የተለያዩ ተሻሽለው የቀረቡ መፍትሔዎችን ይሰጣል ተብሎ ይታመናል ። ለምሳሌ ፤ ይህን ሕግ በመመርኮዝ ፤ የመክፈያ ዓይነቶች የሚታዩና የሚዳሰሱ ብቻ አይደሉም (እንደ ክሬዲት ካርድ) ፤ እንዲሁም የክፍያ ትዕዛዝ ለመስጠት ከፋዩ የሚፈጽማቸው ተከታታይ ድርጊቶች እንደ መክፈያ መንገድ ተገልጸው ይገኛሉ ።

የክፍያ አገልግሎቶች ሕግ ብዙ ዝርዝሮችን የያዘ ውስብስብ ሕግ ነው። ስለዚህ ከዚህ በታች የዋና ዋና አቅርቦቶቹ መካከል ከፊሎቹን ብቻ እናቀርባለን ፦ የእያንዳንዱን የክፍያ ዘዴ አገልግሎት በጥሞና ማወቅና እያንዳንዱን የክፍያ ዘዴ በሕጉ መሰረት ለየብቻ መታይት ይኖርበታል ።

የክፍያ አገልግሎቶች አቅርቦት ለመስጠት የሚደረግ ውል

የክፍያ አገልግሎቶችን የማቅረብ ውል በክፍያ አገልግሎት አቅራቢና በደንበኛ መካከል ይደረጋል ። ሕጉ የክፍያ አገልግሎቶችን ለማቅረብ ውል በጽሁፍ ፤ ግልጽ በሆነና ለመረዳት በሚያስችል ቋንቋ ይዘጋጃል :: ውሉ አንድ ነጠላ የክፍያ ዓይነቶች ወይም በርካታ የክፍያ ሥራዎችን ሊያመለክት ይችላል:: ስለዚህ ደንበኛው አገልግሎቱን ለመቀበል ያለው ፈቃድ ግልጽ መሆን አለበት ።

ውሉ በውስጡ ያሉትን አስፈላጊ ቃላቶች ቀላል እንዲሆኑና አጭር መግለጫ ሊኖረው ይገባል ። እርሱም በተጠናከረና ግልጽ በሆነ መልኩ ይቀርባል ። ደንበኛው ውሉን ከመፈረሙ በፊት አገልግሎት ሰጪው ውሉን እንዲገመግም ዕድል መስጠት አለበት።ደንበኛው ውሉን ከፈረመ በኋላ አገልግሎት ሰጪው የውሉን ግልባጭ እንዲሰጠው መሆን አለበት ።

አገልግሎት ሰጪው የክፍያ አገልግሎት አካል ያልሆኑ ተጨማሪ አገልግሎቶችን ለደንበኛው ሲሰጥ፣ እነዚህ አገልግሎቶች በውሉ ውስጥ ተለይተው መታየት አለባቸው ።

በውሉ ላይ የውል ጊዜ ሲያልቅ አዲስ ውል ሳይፈርም ሊታደስ እንደሚችል ከተገለጸ፣ ያለፈው ውል የውል ማራዘሚያ       ጊዜ       ላይም       ይሠራል       ። የክፍያ አገልግሎት አቅራቢው በሕጉ ውስጥ በዝርዝር እንደተገለጠው በስምምነቱ ውስጥ ያለውን እያንዳንዱን ቁሳቁስ ዝርዝር ለደንበኛው ማሳወቅና በግብይቱ ውስጥ በማንኛውም ምርት ነገር ሸማቹን ማሳሳት የለበትም ።

ለክፍያ አገልግሎት አቅርቦት የመስጠት ውል ስለመጨረስ

ደንበኛው በማንኛውም ጊዜ የክፍያ አገልግሎት አቅራቢውን በማሳወቅ ውሉን ማቋረጥ ይችላል ። የክፍያ ሒሳብ አስተዳደር አገልግሎትን ለማቅረብ ውልን ማቋረጥን በተመለከተ ደንበኛው በውሉ ውስጥ በተገለጠው መሰረት ሒሳቡን ለመዝጋት አስፈላጊውን እርምጃ ካጠናቀቀበት ቀን ጀምሮ የሚቋረጥበት ቀን አምስት የሥራ ቀናት ናቸው ።

የክፍያ አገልግሎት አቅራቢው የክፍያ አገልግሎት ውልን በማንኛውም ጊዜ ለደንበኛው በጽሑፍ በማስታወቅ ሊያቋርጥ እንደሚችልና የማቋረጫው ቀንም ማስታወቂያው ከተላከበት ቀን ጀምሮ ባሉት 45 ቀናት መጨረሻ ላይ ይሆናል ።

የክፍያ ሥራዎችን ስለማከናወን

የክፍያ አገልግሎት አቅራቢ የክፍያ ማዘዣ ከተቀበለ በኋላ ብቻ የክፍያ ሥራን ማከናዎን ይችላል ። ከፋዩ የማስፈጸሚያ ቀኑ ወደፊት የሚሆን የክፍያ ትዕዛዝ ከሰጠ አገልግሎት ሰጪው የወደፊት ክፍያ ከማድረጉ በፊት ከፋዩን የማስገደድ መብት የለውም ።

የክፍያ አገልግሎት ሰጪው ገንዘቡን ለተጠቃሚው (የክፍያ ተቀባይ) ይደርሳል ብሎ የገመተበትን ቀን ጨምሮ ገንዘቡን የሚያስተላልፍበትን ቀን መረጃ ለከፋዩ መስጠት አለበት ፤ የክፍያ አገልግሎት ሰጪው ከተላለፈው ገንዘብ ሌላ ክፍያ አይቀንስም ። የክፍያ አገልግሎት ሰጪውና ተጠቃሚው በሌላ መንገድ ሊስማሙ ይችላሉ ።

ካልሆነ ግን አገልግሎት ሰጪው በተመጣጣኝ ምክንያቶች የክፍያ ክንዋኔውን ላለመፈጸም መብት ይኖረዋል። አንድ አገልግሎት ሰጪ የክፍያ ክንዋኔውን ለመፈጸም ፈቃደኛ ካልሆነ ለደንበኛው ማሳወቅ አለበት ። በማስታወቂያው ውስጥ ፤ የአገልግሎት አቅራቢው የተጠየቀውን የክፍያ ሂደት እንዲያከናውን ፤ ውድቅ የተደረገበትን ምክንያቶች እና ደንበኛው ሊወስዳቸው የሚችላቸውን እርምጃዎች መዘርዘር አለበት ።

የክፍያ አገልግሎት ሰጪው የክፍያ ትዕዛዙን አፈጻጸም ለማስቆም እስከቻለ ድረስ ከፋዩ የሰጠውን የክፍያ ትዕዛዝ ሊሰርዝ ይችላል ።

ምንም ማሳወቂያ ካልተሰጠና የመክፈያ ዘዴው አላግባብ ጥቅም ላይ ከዋለ ፤ የከፋዩ ኃላፊነትና ተጠያቂነት መጠን እንደሚከተሉት ዝርዝር ሁኔታዎች ይሆናል ፤

  1. የተወሰነ የ75 ሸቄልና ለእያንዳንዱ ቀን በቀን 30 ሸቄል በመጨመር ከፋዩ የመክፈያ ዘዴው አስፈላጊ አካል መሰረቁን ወይም መጥፋቱን ካወቀበት ቀን ጀምሮ፣ ወይም የክፍያውን መንገድ አላግባብ መጠቀም ከታወቀበት ቀን ጀምሮ እስከ ማስታወቂያው የሚላክበት ቀን፣ (ክፍያውን ለመጀመሪያ ጊዜ አላግባብ ከተጠቀመ፣ ከፋዩ በ 30 ቀናት ውስጥ ማስታወቂያውን ካደረሰ ከ 450 ሸቄል በላይ ላለው መጠን ተጠያቂ አይሆንም)።
  2. የክፍያው ዘዴዎች አላግባብ ጥቅም ላይ በሚውሉበት ጊዜ የተከናወኑ የክፍያ ሥራዎች ብዛት

ከላይ የተጠቀሰው ቢሆንም በተጨማሪ ፤ ይህ ማስታወቂያ እስካልተሰጠ ድረስ ፤ ከፋዩ የመክፈያ ዘዴዎችን አስፈላጊ አካል ለሌላ ሰው ካቀረበ ፤ አጠቃቀሙ በከፋዩ ስምምነት ወይም በማያውቅበት መንገድ ከተከናዎነ ፤ የከፋዩ ተጠያቂነት የመገደብ ሁኔታ የለም ። ሆኖም ግን ፤

  1. የመክፈያ መንገዱ ወይም የመክፈያ ዘዴውን እያወቁ ለሌላ ሰው እንዲከፍልበት ወይም ክፍያ እንዲቀበልበት ከተስማሙና የመክፈያ ካርዱ ከጥበቃ ለሌላ ሰው ከተሰጠ ለተጠቃሚው እንዲጠቀምበት ፈቃድ ተሰጥቷል ።
  2. ይህ አላግባብ መጠቀሚያነት የሚከናወነው የክፍያው መንገድ ወይም ለሦስተኛ ወገን ለክፍያ አስፈላጊው አካል ከተሰረቀ ወይም ከእርሱ ከጠፋ በኋላ ነው

ከላይ እንደተገለጠው የከፋዩ ተጠያቂነት ውስን ሆኖ ይቆያል ።

በማንኛውም ሁኔታ የክፍያ አገልግሎት ሰጪው ከፋዩ በማንኛውም ጊዜ ማስታወቂያ እንዲሰጥ ወይም የመክፈያ ዘዴውን እንዲሰርዝ የማይፈቅድ ከሆነ፣ ለከፋዩ ምንም ዓይነት ተጠያቂነት አይኖርም ። በክፍያው አላግባብ ጥቅም ላይ ከዋለ ደግሞ ከፋዩ የማጭበርበር ድርጊት የፈፀመ ከሆነ ፤ የተጠያቂነት ገደቡ ሥራ ላይ አይውልም (ሙሉ በሙሉ ወይም ከላይ እንደተገለጠው የከፍተኛው መጠን) ስለዚህ የክፍያ መንገዱን አላግባብ ስለመጠቀም ተጠያቂ ይሆናል ።

ከፋዩ በተጠቃሚው በኩል የክፍያ ማዘዣ ከሰጠ (ለምሳሌ የክፍያው ተቀባይ ፤ ሒሳቡን የመቀነስ ፍቃድ) እና የብድር መጠኑ በከፋዩ ትዕዛዝ መሰረት የተጨመረ ካልሆነ የክፍያ አገልግሎት ሰጪው ልዩነቱን ለከፋዩ ይመልሰዋል ። ከፋዩ በትክክል በተጠየቀው ገንዘብና ከፋዩ ለመክፈል ቃል መግባቱን ባወጀው መጠን መካከል ይቻላል ።

"ከጎደለ ሰነድ ጋር የክፍያ አሠራር" ማለት ከፋያው የተፈረመበት ሰነድ የሌለበት የክፍያ ደብዳቤ ሲሆን፣ የተጠቃሚውን መለያ ፤ የከፋዩን ወይም የመክፈያ ዘዴውን ፤ የግብይቱን መጠንና ግብይቱ የተፈፀመበትን ቀን (ለምሳሌ የክሬዲት ካርድ መረጃን በስልክ በማስተላለፍ የሚደረግ ክፍያ) የሌለበት ክፍያ ማለት ነው ። የክፍያ ማስታወቂያው ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ ከፋዩ የክፍያውን ሥራ የፈጸመው በጎደለ ሰነድ እንዳልሆነ ወይም የሚከፈለው ገንዘብ ያለፈቃድ መጨመሩን ለክፍያ አገልግሎት ሰጪው ካሳወቀ፣ የክፍያ አገልግሎት ሰጪው የክፍያውን መጠን ለከፋዩ ይመልሳል ።

ከፋዩ ለክፍያ አገልግሎት አቅራቢው በማሳወቅ ሒሳቡን የመክፈል ዕድሉን በማንኛውም ጊዜ ሊሰርዝ ይችላል። እንዲሁም ከፋዩ ለክፍያ አገልግሎት ሰጪው በሰጠው ፈቃድ መሰረት የተወሰነውን ክፍያ የመሰረዝ መብት አለው ።ይህም ለክፍያ አገልግሎት ሰጪው ማሳወቂያው ከክፍያ ቀን ጀምሮ ከሶስት የሥራ ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ከሆነ ።

የክፍያ አገልግሎት ሰጪው በከፋዩ የተሰጠውን ፍቃድ ከተላለፈና ከፋዩ ከፈቀደው በላይ ካስከፈለው ፤ የክፍያ አገልግሎት ሰጪው የተወሰደውን የክፍያ ልዩነቱን መመለስ አለበት ።

የክፍያ አገልግሎት ሰጪው የክፍያ ትዕዛዙን ሊሰርዝ ወይም የክፍያ ትዕዛዙን በተጠቃሚው (ክፍያውን የሚቀበለው) ጥያቄ መሠረት ላያከናውን ይችላል። ነገር ግን የክፍያ አገልግሎት አቅራቢው ክፍያ አለመፈጸሙን ወዲያውኑ ለከፋዩ ማሳወቅና ያልተከፈለበትን ምክንያት መግለጽ አለበት ።

ልዩ የመክፈያ መንገዶች (የተጠራቀመ የዋጋ ክፍያ ፤ የክፍያ ካርድ) ልዩ ድንጋጌዎች ፤ ደንቦችና ከአንዳንድ የክፍያ አገልግሎቶች ሕግ ድንጋጌዎች ነፃ መሆኑን ያስቀምጣሉ። እነዚህ ዓይነቶች የክፍያ ዘዴዎችም ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል ፤

  1. "የተጠራቀመ ገንዘብ መክፈል" በዚህ ዓይነቱ የመክፈያ ዘዴ መሙላት የምንችለው የገንዘብ መጠን 1500 ሼቄል ነው ፤ እነዚህ የሞላናቸው ገንዘቦች እንደገና ሊሞሉ የማይችሉና ለአንድ የተወሰነ ከፋይ ጥቅም ብቻ የማይውሉና የዕዳ መክፈያው ወዲያውኑ ከተጠራቀመው ቀሪ ሂሳብ ይወርዳል እንጅ ተቆራርጦ በየወሩ መክፈል አይቻልም ።
  1. የሚከተሉት ሁኔታዎች የተሟሉበት የክፍያ ካርድ ዓይነት ዘዴዎች ደግሞ ፤ (1) የግል ላልሆነ የክፍያ አገልግሎት የሚሆን ፤ (2) የገንዘብ ዕርዳታ አካል ሆኖ በመንግሥታዊ አካል ወይም ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ለዕርዳታ የተሰጡ ከሆነ ፤ (3) እንደገና ገንዘብ መሙላት የሚቻልበት ሆኖም ግን በማንኛውም ጊዜ መሙላት የሚችለው የገንዘብ መጠን ከ 1500 ሼቄል የማይበልጥ ፤ (4) ከፋፍሎ የመክፈል ዕድል ሳይኖረው ወዲያውኑ ከካርዱ የሚያስፈልገው ክፍያ ይወርዳል ፤ (5) የክፍያ ማዘዣውን ካርድ በአካል መልክ ብቻ በማቅረብ መግዛት የሚቻልበት ። (6) ከተወሰኑ አቅራቢዎች ነጋዴዎች ወይም አገልግሎት ሰጭዎች ብቻ ለመግዛት የሚያስችል ።

እነዚህን የመክፈያ መንገዶች በተመለከተ ፤ ሕጉ ያስቀመጠውን ልዩ መመሪያዎች መመልከት ያስፈልጋል ።

ቼኮች

ምንም እንኳን ነጋዴዎች ቼኮችን የመቀበል ግዴታ ባይኖርባቸውም፤ በቼክ ክፍያ መፈጸም እስከ አሁን የተለመደ መንገድ ነው። ሆኖም ግን ፤ ማንኛውም ሸማች በቼክ የባንክ ቼክ በሚከፍልበት ጊዜ አንዳንድ ነገሮችን ልብ ማለት አለበት ፤ በቼኮች ክፍያ አንድ ሰፊና የተለመደ ስህተት አለ ። ይህም በቼኩ ላይ "ሁለት የመስመሮችን" ምልክቶች ካደረግንበት ይህን ቸክ በሌላ መንገድ መጠቀም እንደማይቻል ያገለግላል :: ይህም ማለት በቼክ የከፈለውን ሰው ከሌላ አደጋ ያርቃል ማለት ነው (ቸኩን ወደ ሌላ ሰው እንዳይዘዋወር ማድረግ እንደማለት) ።

ነገር ግን ፤ ይህ ቼክ ላይ የምናሰምረው መስመር ፍቹ ፤ ገንዘቡን ለመቀበል ቼኩን ወደ ባንክ ማስገባት አለብን እንጅ ጥሬ ገንዘብ መቀበል አይቻልም ማለት ነው ። ቼኮች ወደ ሌላ ሰው እንዳይተላለፉ ለማድረግ ፤ ከባንክ ቼኩን ሲያስመጡ ከቼኩ ላይ "ቼኩ ለተሰጠው ሰው" ሚለው ቃል እንዲኖርና "የተሰጠው" የሚለውን ሰርዘን "የተከፈከው ለ" የሚለውን ቃል ማጻፍ አለብን ። በተጨማሪም ፤ የተጠቃሚውን ስምና የገንዘብ መጠኑን ከሞሉ በኋላ በመጨረሻ"ብቻ" የሚለውን ቃል መጨመር ያስፈልጋል ።

መጀመሪያ የሕግ ምክር ሳያገኙ ቼኮችን መሰረዝ አይመከርም ። ሸማቹ ቼኮችን የመሰረዝ መብት ያለው በጣም ባልተለመዱ ጊዜዎች ብቻ ነው ፤ ስለዚህ እያንዳንዱን እርምጃ ከመውሰድዎ በፊት መመሪያና ምክር ማግኘት አስፈላጊ ነው።

 

 

በዚህ የመምሪያ መጽሔት ውስጥ የቀረበው መረጃ አጠቃላይ መረጃ ብቻ ነው ፤ ግን ሕጋዊ ምክርን የሚተካ አይደለም እና ያለ ተገቢ ምክር ብቻዉን መታመን የለበትም.
ይህ መምሪያ ሰኔ ወር 2023 ዓ.ም. ያለውን መረጃ በሕጉ እና ደንቡ ላይ በመመርኮዝ ተሻሽሏል ።
አስገዳጅ የሚሆነው የሕጉ እና የደንቡ ጽሑፍ ነው።