ድርጅቱ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ እና ከአንድ መቶ ለሚበልጡ ዓመታት የሠራተኞች ማህበር ድርጅት በእስራኤል ውስጥ የሠራተኞችን እና የጡረተኞችን ሁኔታ ለማጠናከር ሥራውን እየሰራ ይገኛል ። በሠራተኛ ማኅበሩ ዘርፍ ከሚደረገው ሰፊ እንቅስቃሴ ጎን ለጎን ፤ የሠራተኞች ማህበር ለአባላቶቹ ከሞላ ጎደል ሁሉንም የሕይወት ዘርፎች የሚዳስሱ ሰፊና ልዩ ልዩ አገልግሎትን ያቀርባል። ከትምህርት ማስተማር ጀምሮ ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን እስከ ባህላዊ እና መዝናኛ ጊዜዎችን በማስተዋወቅና ከሥራ ቦታ ውጪም ቢሆን ለእያንዳንዳችሁ ተጨማሪ አገልግሎቶችን እያዘጋጀን መስጠታችንን እንቀጥላለን ።
የሠራተኞች ማህበር ለደህንነትህ ከሚሠራኛው አንጋፋ ድርጅቶች አንዱ የሠራተኞች የሸማቾች ማህበርን አቋቁሟል። የዚህ ድርጅት ዋና ዓላማው ኢ-ፍትሃዊነትን መከላከል እና አንድን ሸማች ግለሰብ በደንቡ መሰረት ያለውን መብቶች ማስጠበቅ ይሆናል ። በተጨማሪም የተለያዩ አግባብ ያላቸውን ሕጎችን ማስተዋወቅ ፤ የዳሰሳ ጥናቶችን ማድረግ ፤ የመስክ ጥናታና ቁጥጥሮችን እና የዋጋ ንፅፅር ምርመራዎችን ማካሄድ ። በሸማቾች ጉዳይ ላይ የሚደርስባቸውን የተለያዩ ቅሬታዎችን ማስተናገድ እና የመብት አጠቃቀምን ማስረዳትን ያጠቃልላል ። የሠራተኞች ማህበር ድርጅት ተወካይ ባለስልጣኖች በሁሉም የአገራችን ክፍሎች ተቋቁመው ይገኛሉ:: ክእነርሱም ተጨማሪና አስፈላጊውን መረጃና አገልግሎት መቀበል ትችላላችሁ ።
በተለያዩ የሸቀጣ አሸቀጥ ድርጅቶች ጉዳት ደርሶብዎታል? የስድብ ጉዳት ደርሶብዎታል ? እኛን ለማነጋገርና አስፈላጊውን ምክር ለመቀበል በ -*2383 መደወል ይቻላል ወይም መተግበሪያ (በአፕሊኬሽን ) መጠቀም ይቻላል ።
የሠራተኞች ማህበር ድርጅት ከኑሮ ውድነት ጋር በሚያደርገው ትግል ግንባር ቀደም ሚና እየተጫወተ ይገኛል:: የሸማች ሠራተኞች ማህበር ደግሞ ይህን ትግል በሌላ መልኩ ለመመልከት የሚረዱ የተለያዩ መፍትሔዎችንም ይሰጣል ። ይህ የመመሪያ መጽሔት የሚደሳችሁን መብቶች በተመለከተ ታማኝ ፤ በፈለጉት ሰዓት የሚገኝና የተስተካከለ ወቅታዊ መረጃዎችን እንድታገኙ ይረዳችኋል ።
የሠራተኞችን አንድነት ድርጅት በመጠቀም ለእናንት እና ለእስራኤል ማህበረሰብ በሙሉ የማጠናከር-ሥራችንን እንቀጥላለን ።
ከአክብሮት ጋር አርኖን ቤን ዳቪድ
የሠራተኞች አንድነት ማህበር ዋና ሥራ አስኪሃጅ