በአንድ ጎን ብቻ የተዘጋጁ ዉሎች ማለት “ቁጥራቸው ባልታወቀ ሰዎች ወይም በማንነታቸው በማይታወቁ ሰዎች መካከል ለሚደረጉት ብዙ ውሎች ፣ በአንድ ተዋዋይ ወገን ውሉ በሙሉ ወይም በከፊል የተወሰነው የውል ሰነድ ነው " ይህ ሻጭ ለሸማቹ ውል የሚያቀርብበት ሁኔታ አስቀድሞ በሻጩ በተወሰነው ስምምነት ዓይነት (ይህ ሁኔታ ጥቅም ላይ የሚውልበት ሁኔታ ለምሳሌ በግንኙነቶች መስክ ከትላልቅ ኩባንያዎች ጋር ውል ሲደረግ ፤ የባንክ አገልግሎት፣ የኋይል አቅርቦት) ጉልበት የሚሰጠው ሰነድ ማለት ነው ። የዚህ ዓይነት ውልን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች የተመሰረቱት በአንድ ጎን ብቻ የተዘጋጁ ዉሎችን በሚመለከተው ሕግ መሰረት ነው። ሕጉም የተደነገገው በ 1982 ዓ.ም ሲሆን፣ ዓላማው ሸማቾችን ከአደጋ ከሚያስከትሉ ሁኔታዎች ለመጠበቅ ነው። ይህም ሲባል በፓርቲዎች መካከል ባለው የመረጃና የስልጣን ክፍተት ምክንያት የሸማቹ ህብረተሰብ ለችግር መዳረጉን በመረዳት ነው ።
መድሏዊ ድርጊቶች ማለት ፤ ሸማቾችን የሚጎዳ ወይም ለነጋዴው የኢ-ፍትሃዊ ጥቅም የሚያደላና ሸማች የሚደርሱትን ጥቅሞች እንዲያጣ የሚያደርግ ሁኔታ ነው ።
ከዚህ በታች በሕግ የተደነገጉ ሁኔታዎች መድሎ ናቸው ተብሎ የሚታመኑ አንዳንድ ምሳሌዎችን ያቀርባሉ ።
ፍርድ ቤቱና የፍርድ መስጫ ተቋሞች ለሚደረጉ ዉሎች፣ ልዩና በአንድ ወጥ ውል ውስጥ ያሉ መጥፎ ሁኔታዎችን ለመሰረዝ ወይም ጉዳት እንዳይደርስባቸው እንዲቀይሩ ተፈቅዶላቸዋል ።
በዚህ የመምሪያ መጽሔት ውስጥ የቀረበው መረጃ አጠቃላይ መረጃ ብቻ ነው ፤ ግን ሕጋዊ ምክርን የሚተካ አይደለም እና ያለ ተገቢ ምክር ብቻዉን መታመን የለበትም.
ይህ መምሪያ ሰኔ ወር 2023 ዓ.ም. ያለውን መረጃ በሕጉ እና ደንቡ ላይ በመመርኮዝ ተሻሽሏል ።
አስገዳጅ የሚሆነው የሕጉ እና የደንቡ ጽሑፍ ነው።