በእስራኤል አገር ውስጥ የተደነገጉ ብዙ ሕጎች የሸማቹን መብት ያስከብራሉ (የተመረጠ የሸማቾች ሕግ ገጽ 54 ላይ ያለውን ክፍል መመልከት ይቻላል) ። ከእነዚህም ሕጎች መካከል በጣም አስፈላጊ የሆነው አንዱ የሸማቾች ጥበቃ ሕግ 1981 ነው ፤ ይህ ሕግ የተገልጋዮችን መብት የሚወስኑ እና በነጋዴዎች ላይ የሚጣሉትን ግዴታዎች የሚወስኑ ብዙ ድንጋጌዎችን ያጠቃለለ ነው። ነገር ግን እነዚህ መብቶች እና ግዴታዎች የሚተገበሩት በ "ሻጮችና በሸማቾች " መካከል ባለው ግንኙነት ሲሆን፣ ይህም የሚሆነው የተደነገገው ሕግ የሚሰጠውን መመሪያ በመመርኮዝ ነው ።
በተደነገገው ሕግ መሠረት "ሻጭ" ማለት የግል ንብረቱን የሚሸጥ ወይም የሽያጭ አገልግሎትን በንግድ በኩል የሚሰጥ ሰው እንደሆነ ይገልጻል ። ንብረት ሲባል ለምሳሌ የተለያዩ ምርቶች ፤ የገንዘብ ግብይቶች ፤ የመሬት ወይም የቤት ሽያጭና መብቶች ሊሆኑ ይችላሉ ። "ንግድ" ማለት ደግሞ ካለው የግል ንብረት በከፊሉ የሚሸጥ ማለት ነው ። ስለዚህ ንብረቱን ሕጉ በፈቀደው መሠረት ያለ ምንም የግብይት ድርጅት ባጋጠመው መንገድ ብቻ የሸጠ የገዥና የሻጮች ሕግ አይመለከተውም ።
ሕጉ “ሸማቾች” የሚለውን ቃል ሲተነትነው ፤ ለግል መጠቀሚያው ወይም ለቤተሰብ መጠቀሚያ በማሰብ ቤት የሚገዛ ፤ ለቤተሰብ አገልግሎት የሚውል ንብረት የሚገዛ ወይም በንግድ ሥራው ውስጥ አገልግሎት የሚቀበል ሰው ማለት ነው ። ልብ ማለት ያለብን ይህ ሕግ የሚያመለክተው በሸማቾች ጥቅም ጥበቃ ሕግ መሰረት "ሸማች" ተብሎ ያልተገለጠ ንብረትን የገዛ ወይም ከንግድ ሥራ የሚያገለግል አገልግሎት የሚቀበል ሰው ሲሆን ሕጉ ድንጋጌዎችም በዚህ ሸማች ግለሰብ ላይ ተፈጻሚነት የላቸውም ።
የሸማቾች ጥቅም ጥበቃ ሕግ እንደሚወስነው ከሆነ ፣የአገሪቱም ሕግ ልክ እንደ አንድ ድርጅት በመቆጠር ልዩነት እንደሌለባቸው ያስታውቃል ። በሌላ በኩል ሕጉ ብዙ ዓይነት ነጋዴዎችን አያካትትም - የሕጉ ድንጋጌዎች በደንበኞች እና በባንክ ኮርፖሬሽኖች መካከል ያለውን ግንኙነት በባንክ ሕግ (የደንበኛ አገልግሎት) መሰረት እንደማይተገበሩ ተወስኗል ። በኢንሹራንስ ንግድ ቁጥጥር ሕግ መሠረት በሸማቾች እና በኢንሹራንስ ሰጪ ወይም በኢንሹራንስ ወኪል መካከል ስላለው ግንኙነት እና በደንበኞች እና በገንዘብ አገልግሎት አቅራቢዎች መካከል ባለው የቁጥጥር የገንዘብ አገልግሎቶች ቁጥጥር ሕግ ላይ እንደ ገንዘብ ማጠራቀሚያ ያሉ ድርጅቶችን ይመለከታል ።
በዚህ የመምሪያ መጽሔት ውስጥ የቀረበው መረጃ አጠቃላይ መረጃ ብቻ ነው ፤ ግን ሕጋዊ ምክርን የሚተካ አይደለም እና ያለ ተገቢ ምክር ብቻዉን መታመን የለበትም.
ይህ መምሪያ ሰኔ ወር 2023 ዓ.ም. ያለውን መረጃ በሕጉ እና ደንቡ ላይ በመመርኮዝ ተሻሽሏል ።
አስገዳጅ የሚሆነው የሕጉ እና የደንቡ ጽሑፍ ነው።