ሻጩ በማንኛውም መንገድ ለምሳሌ የተለያዩ ነገሮችን በማድረግ ፤ በተፈጠሩ ስህተቶች ሸማቹን ማሳሳት የተከለከለ ነው ። ሕጉ ይህ ስህተት የማይፈጠርባቸውን ሁኔታዎች በበርካታ ምሳሌዎችን አማካኝነት ያቀርባል:: የምርት አቅርቦት ወይም የአገልግሎት አቅርቦት ቀን ፤ የምርት ወይም የአገልግሎት ዓይነት ፤ የምርትን የክብደት ሚዛን በተመለከተ ፤ ምርቱ የተመረተበት ቦታን በተመለከተ ፤ የአገልግሎት ሰጪው ማንነት ፤ የመለዋወጫ ዕቃዎች መኖር እና ወ.ዘ.ተ. ። እነዚህ ምሳሌዎች ብቻ ናቸው በአንዳንድ ሁኔታዎች የተሳሳተ መረጃ መስጠት ወይም ሙሉ መረጃ ለገብይው አለማቅረብ ልክ ገብይውን እንደማሳሳት እና የተሳሳተ መረጃ እንደመጠቀም ተደርጎ ሊታይ የሚቻልበት ሁኔታዎች ሊኖሩ ይችላሉ ።
የተከለከሉ ማስታዎቂያዎች
በማስታወቂያ በኩል ማታለል የተለመደ ክስተት መሆኑ ይታዎቃል ፤ ስለዚህ ሕጉ ይህን ድርጊት የተከለከለ መሆኑን በግልፅ ይናገራል ። የምርቱን ጥራት እና ባህሪ በተመለከተ ማሳሳት ብቻ ሳይሆን፣ ማስታወቂያ መሆኑን በማስታወቅ ማሳሳትን ጨምሮ የተከለከለ ነው - ይህም ማለት ማስታወቂያን ልክ እንደ የተፃፈ ሰነድ አድርጎ ማቅረብም አይፈቀድም ። አንዳንድ የተፃፉ ሰነዶች የማስታዎቂያ ጽሁፎች መሆናቸውን በይፋ ሳይነገሩ በውስጣቸው ያለው መልዕክት እውነትኛ ቢሆንም ቅሉ፣ የማስታዎቂያ ጹሁፎች ሆነው ይቀርባሉ ። -ይህን በተመለከተ በሬዲዮ ፤ በጋዜጣ ፤ በቴሌቪዚያ ፤ በኢንተርኔት አማካኝነተ ከሚደረጉ ማስታዎቂያዎች ጋር ምንም ዓይነት ልዩነት የለውም ። በተጨማሪም ለአቅም አዳም ላልደረሱ ልጆች ላይ ያተኮሩ ማስታዎቂያዎች ወይም የግብይት ዘዴዎች በልጆች ላይ ተጽኖ የሚያሳድሩና ውሳኔያቸውን ሊያዛቡባቸው ስለሚችሉ ይህ ዓይነት ድርጊት የተከለከለ ነው ።
የምርት ወይም የአገልግሎት አቅርቦት ቦታን በተመለከተ ማታለል የተከለከለ ነው ።
አሳሳች ማስታዎቂያዎችን ይፋ የማድረግ መመሪያ በተጨማሪ የሸማቾች ጥበቃ ሕጉ ንብረቱን ወይም አገልግሎቱን በሚሰጥበት ቦታ (የይሁዳና የሰማርያ ክልልን ጨምሮ) ሸማቾችን ማሳሳት የተከለከለ መሆኑን እና እንዲሁም በዚህ ረገድ ሸማቹን ላሳሳቱ እና ምርቱን ወደ ስምምነት ቦታ ላላቀረቡለት ሻጮች እስከ 10,000 ሸቄል ድረስ የማካካሻ ዋጋ ሊከፍሉ ይችላሉ (ስለማካካሻ ምሳሌዎች በገጽ 49 ላይ ተጨማሪ መረጃን ይመልከቱ)።
ማታለል ወይም ብዝበዛ ቢፈጠር ምን ታደርጋለህ ?
አንድ ሸማች አንድን ምርት ወይም አገልግሎት ሲገዛ እና እንደተታለለ ግልጽ ቢሆንለት ፤ ሸማቹ በአንዳንድ ሁኔታዎች ግብይቱን እንዲሰርዝ ሕጉ ይፈቅዳል ። የተደረገውን ግብይት ለመሰረዝ ያሉትን ምክንያቶች አሳስተውኛል ለሚለው ጥያቂ መልሱ ቀላል አይደለም ፤ ስለዚህ ሸማቾች በመጀመሪያ ተገቢውን ምክር ሳይቀበሉ የእራሳቸውን ምክንያቶች ብቻ ተመርኩዘው ግብይቱን መሰረዝ አይመከርም ። አሳስተውናል ብላችሁ የምታስቡ ከሆነ በመላ አገሪቱ ተሰማርተው ያሉትን የሂስታድሩት አማካሪ ሠራተኞች ወይም በቴል አቪቭ የሚገኘውን የድርጅቱን ዋና መሥሪያ ቤት ምክር እና መመሪያ መቀበል ትችላላችሁ። (ከዚህ በታች ያለውን ዝርዝር ከገጽ 58-59 ይመልከቱ)።
በዚህ የመምሪያ መጽሔት ውስጥ የቀረበው መረጃ አጠቃላይ መረጃ ብቻ ነው ፤ ግን ሕጋዊ ምክርን የሚተካ አይደለም እና ያለ ተገቢ ምክር ብቻዉን መታመን የለበትም.
ይህ መምሪያ ሰኔ ወር 2023 ዓ.ም. ያለውን መረጃ በሕጉ እና ደንቡ ላይ በመመርኮዝ ተሻሽሏል ።
አስገዳጅ የሚሆነው የሕጉ እና የደንቡ ጽሑፍ ነው።